ዘኍል 25:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ያንንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። እስራኤላዊውንም ሰውና ሴቲቱን ሁለቱንም ሆዳቸውን ወጋቸው። ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተከለከለ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ፤ ጦሩንም ወርውሮ እስራኤላዊውንና ሴቲቱን አጣምሮ ወጋቸው። ከዚያም በእስራኤላውያን ላይ የወረደው መቅሠፍት ተከለከለ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ሰውየውና ሴቲቱ ወዳሉበት ድንኳን ገባ፤ ሁለቱንም በአንድነት በጦር ወግቶ ገደላቸው፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያንን በማጥፋት ላይ የነበረው መቅሠፍት ቆመ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ያንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። ሁለቱንም እስራኤላዊውን ሰውና ምድያማዊቱን ሴት ሆዳቸውን ወጋቸው፤ ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተወገደ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ያንንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። እስራኤላዊውንም ሰውና ሴቲቱን ሁለቱን ሆዳቸውን ወጋቸው። ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተከለከለ። ምዕራፉን ተመልከት |