የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው፤ የሞ​ዓብ አለ​ቆ​ችም በበ​ለ​ዓም ዘንድ አደሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በለዓምም፣ “እግዚአብሔር የሚሰጠኝን መልስ አመጣላችኋለሁና የዛሬን ሌሊት እዚሁ ዕደሩ” አላቸው። ስለዚህም የሞዓብ አለቆች ከርሱ ዘንድ ቈዩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፥ ጌታም እንደሚነግረኝ እመልስላችኋለሁ”፤ የሞዓብም አለቆች በበለዓም ዘንድ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በለዓምም “እዚሁ ዕደሩና ነገ ጧት እግዚአብሔር የሚነግረኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ በዚህ ዐይነት የሞአባውያን መሪዎች ከበለዓም ጋር ቈዩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፥ እግዚአብሔርም እንደሚነግረኝ እመልስላችኋለሁ አላቸው፤ የሞዓብም አለቆች በበለዓም ዘንድ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 22:8
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ንጉ​ሡን፥ “የቤ​ት​ህን እኩ​ሌታ እን​ኳን ብት​ሰ​ጠኝ ከአ​ንተ ጋር አል​ገ​ባም፤ በዚ​ህም ስፍራ እን​ጀ​ራን አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም፤


ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።


አንተ ተክ​ለ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ሥር ሰድ​ደ​ዋል፤ ወል​ደ​ዋል አፍ​ር​ተ​ው​ማል፤ በአ​ፋ​ቸ​ውም አንተ ቅርብ ነህ፤ ከል​ባ​ቸው ግን ሩቅ ነህ።


ሕዝብ እን​ደ​ሚ​መጣ ወደ አንተ ይመ​ጣሉ፤ እንደ ሕዝ​ቤም በፊ​ትህ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ፤ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባ​ቸ​ውም ጣዖ​ታ​ትን ይከ​ተ​ላ​ልና።


እር​ሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራ​እይ እገ​ለ​ጥ​ለ​ታ​ለሁ፤ ወይም በሕ​ልም እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።


በለ​ዓ​ምም መልሶ የባ​ላ​ቅን አለ​ቆች፥ “ባላቅ በቤቱ የሞ​ላ​ውን ወር​ቅና ብር ቢሰ​ጠኝ፥ በት​ንሹ ወይም በት​ልቁ ቢሆን የአ​ም​ላ​ኬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እተ​ላ​ለፍ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ አሁን አን​ዳ​ችን ነገር ለመ​ና​ገር እች​ላ​ለ​ሁን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ቃል እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለው።


የሞ​ዓብ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የም​ድ​ያም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም የም​ዋ​ር​ቱን ዋጋ በእ​ጃ​ቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለ​ዓ​ምም መጡ፤ የባ​ላ​ቅ​ንም ቃል ነገ​ሩት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ በለ​ዓም መጥቶ፥ “እነ​ዚህ በአ​ንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች እነ​ማን ናቸው?” አለው።


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን መልሶ፥ “በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ ያደ​ረ​ገ​ውን እና​ገር ዘንድ የም​ጠ​ነ​ቀቅ አይ​ደ​ለ​ምን?”


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “በመ​ሥ​ዋ​ዕ​ትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢገ​ለ​ጥ​ልኝ፥ ቢገ​ና​ኘ​ኝም እሄ​ዳ​ለሁ፤ የሚ​ገ​ል​ጥ​ል​ኝ​ንም ቃል እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለው። ባላ​ቅም በመ​ሠ​ዊ​ያው ዘንድ ቆመ፤ በለ​ዓም ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይጠ​ይቅ ዘንድ አቅ​ንቶ ሄደ።


ባላቅ በቤቱ የሞ​ላ​ውን ብርና ወርቅ ቢሰ​ጠኝ፥ መል​ካ​ሙን ወይም ክፉ​ውን ከልቤ ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እተ​ላ​ለፍ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላ​ክ​ሃ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ አል​ተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸ​ው​ምን?