Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 24:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ባላቅ በቤቱ የሞ​ላ​ውን ብርና ወርቅ ቢሰ​ጠኝ፥ መል​ካ​ሙን ወይም ክፉ​ውን ከልቤ ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እተ​ላ​ለፍ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላ​ክ​ሃ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ አል​ተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸ​ው​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ‘ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር የሚለውን ብቻ ከመናገር በቀር ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ውጭ በራሴ ሐሳብ በጎም ሆነ ክፉ ማድረግ አልችልም።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ‘ባላቅ በቤቱ የሞላውን ብርና ወርቅ ቢሰጠኝ፥ በራሴ ፈቃድ መልካምን ወይም ክፉን ነገር ለማድረግ የጌታን ቃል መተላለፍ አልችልም፤ ጌታ የተናገረውን እርሱን እናገራለሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ‘ባላቅ በቤተ መንግሥቱ ያለውን ብርና ወርቅ ሁሉ ቢሰጠኝ እንኳ በራሴ ፈቃድ ደግ ወይም ክፉ ነገር አደርግ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል መተላለፍ አልችልም፤ የምናገረው እግዚአብሔር እንድናገር የነገረኝን ነገር ብቻ ነው’ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 24:13
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ንጉ​ሡን፥ “የቤ​ት​ህን እኩ​ሌታ እን​ኳን ብት​ሰ​ጠኝ ከአ​ንተ ጋር አል​ገ​ባም፤ በዚ​ህም ስፍራ እን​ጀ​ራን አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም፤


ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።


ሙሴም አለ፥ “ይህን ሥራ ሁሉ አደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ላከኝ እንጂ ከልቤ እን​ዳ​ይ​ደለ በዚህ ታው​ቃ​ላ​ቸሁ።


በለ​ዓ​ምም መልሶ የባ​ላ​ቅን አለ​ቆች፥ “ባላቅ በቤቱ የሞ​ላ​ውን ወር​ቅና ብር ቢሰ​ጠኝ፥ በት​ንሹ ወይም በት​ልቁ ቢሆን የአ​ም​ላ​ኬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እተ​ላ​ለፍ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ በለ​ዓም በሌ​ሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠ​ሩህ ዘንድ መጥ​ተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ታደ​ር​ጋ​ለህ” አለው።


እር​ሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው፤ የሞ​ዓብ አለ​ቆ​ችም በበ​ለ​ዓም ዘንድ አደሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች