Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አንተ ተክ​ለ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ሥር ሰድ​ደ​ዋል፤ ወል​ደ​ዋል አፍ​ር​ተ​ው​ማል፤ በአ​ፋ​ቸ​ውም አንተ ቅርብ ነህ፤ ከል​ባ​ቸው ግን ሩቅ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንተ ተክለሃቸዋል፤ ሥርም ሰድደዋል፤ አድገዋል፤ ፍሬም አፍርተዋል። ሁልጊዜ አንተ በአፋቸው ላይ አለህ፤ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ተክለሃቸዋል፤ ሥርም ሰድደዋል፤ አድገዋል ፍሬም አፍርተዋል፤ በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፥ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አንተ ተክለሃቸዋል፤ እነርሱም ሥር ሰደዋል፤ አድገውም ፍሬ ያፈራሉ፤ በአፋቸው ያከብሩሃል፤ ልባቸው ግን ከአንተ የራቀ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ተክለሃቸዋል፥ ሥር ሰድደዋል፥ አድገዋል አፍርተውማል፥ በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፥ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 12:2
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከ​ን​ፈ​ሮቹ ያከ​ብ​ረ​ኛ​ልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከ​ንቱ ያመ​ል​ኩ​ኛል፤ ሰው ሠራሽ ትም​ህ​ር​ትም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤


እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፤ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።


‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤


ለበ​ዓ​ልም በማ​ጠ​ና​ቸው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ለራ​ሳ​ቸው ስለ ሠሩ​አት ስለ እስ​ራ​ኤ​ልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተ​ከ​ለሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፉን ነገር ተና​ግ​ሮ​ብ​ሻል።


ሕዝብ እን​ደ​ሚ​መጣ ወደ አንተ ይመ​ጣሉ፤ እንደ ሕዝ​ቤም በፊ​ትህ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ፤ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባ​ቸ​ውም ጣዖ​ታ​ትን ይከ​ተ​ላ​ልና።


እን​ዲህ በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የሠ​ራ​ሁ​ትን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፥ የተ​ከ​ል​ሁ​ት​ንም እነ​ቅ​ላ​ለሁ፤ ይኸ​ውም በም​ድር ሁሉ ነው።


እርሱ ግን እንዲህ አላቸው “ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤


በዚ​ህም ሁሉ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ ይሁዳ በሐ​ሰት እንጂ በፍ​ጹም ልብዋ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰነ​ፎ​ችን ሥር ሰድ​ደው አየ​ኋ​ቸው፥ በድ​ን​ገ​ትም መኖ​ሪ​ያ​ቸው ጠፋች።


ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፣ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለምን ዝም ትላለህ?


ድሆ​ችን ከከ​ተ​ማ​ውና ከገዛ ቤቶ​ቻ​ቸው አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው የሕ​ፃ​ና​ት​ንም ነፍስ እጅግ አስ​ጮሁ፤


በመ​ኝ​ታ​ቸው ላይ ሆነው ያለ​ቅሱ ነበር እንጂ በል​ባ​ቸው ወደ እኔ አል​ጮ​ኹም፤ ስለ እህ​ልና ስለ ወይን ይገ​ዳ​ደሉ ነበር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች