አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።
ዘኍል 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በባሕር በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የኤሜሁድ ልጅ ኤሌሳማ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምዕራብ በኩል፤ የኤፍሬም ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የኤፍሬም ሕዝብ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በምዕራብ በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስተምዕራብ በኩል በኤፍሬም ክፍል ዓርማ ሥር በየቡድናቸው ይሰፍራሉ፤ የኤፍሬም ነገድ መሪ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሻማዕ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምዕራብ በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበረ። |
አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።
እያለቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማጽናናት አመጣቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስሄዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።”
የምናሴ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች- እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥
የኤፍሬምም ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊቶቻቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የኣሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ አለቃ ነበረ።
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የኤሚሁድ ልጅ የኤሊሳማ መባ ይህ ነበረ።
ውበቱ እንደ ላም በኵር ነው፤ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፤ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፤ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።