የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 23:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ላ​ቆ​ች​ንና ኀይ​ለ​ኞ​ችን አሕ​ዛብ ከፊ​ታ​ችሁ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የተ​ቋ​ቋ​ማ​ችሁ በፊ​ታ​ችሁ ማንም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እግዚአብሔር ታላላቅና ኀያላን ሕዝቦችን ከፊታችሁ አሳድዶ አስወጥቷቸዋል፤ እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ታላላቆችንና ኃይለኞችን አሕዛብ ከፊታችሁ አሳድዶአቸዋል፤ እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ ታላላቅና ብርቱዎች የሆኑትን ሕዝቦች እግዚአብሔር ነቃቅሎ አባሮላችኋል፤ እናንተን እስከ ዛሬ ድረስ ሊቋቋማችሁ የቻለ ማንም የለም፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር ታላላቆችንና ኃይለኞችን አሕዛብ ከፊታችሁ አስወጥቶአል፥ እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 23:9
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚ​ህም በኋላ በዓ​መቱ ወልደ አዴር ሶር​ያ​ው​ያ​ንን ቈጠ​ራ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ይዋጋ ዘንድ ወደ አፌቅ ወጣ።


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በዚህ ምድር የነ​በ​ሩ​ትን አሕ​ዛብ ከሕ​ዝ​ብህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ያሳ​ደ​ድህ፥ ለወ​ዳ​ጅ​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም ዘር ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሰ​ጠ​ሃት አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?


መል​አኬ በፊ​ትህ ይሄ​ዳ​ልና፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ያገ​ባ​ሃል፤ እኔም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ነገር ግን እስ​ክ​ት​በዛ፥ ምድ​ር​ንም እስ​ክ​ት​ወ​ርስ ድረስ ጥቂት በጥ​ቂት አባ​ር​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ኢያ​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በተራ ተቀ​ብ​ለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ፊት አስ​ወ​ጥቶ ወደ ሰደ​ዳ​ቸው ወደ አሕ​ዛብ ሀገር ከእ​ነ​ርሱ ጋር አገ​ቡ​አት፤ እስከ ዳዊት ዘመ​ንም ነበ​ረች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ ያወ​ጣል፤ ከእ​ና​ን​ተም የሚ​በ​ል​ጡ​ትን፥ የሚ​በ​ረ​ቱ​ት​ንም አሕ​ዛብ ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።


ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ስማ​ቸ​ው​ንም ከዚያ ቦታ ያጠ​ፋል፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ማንም ከፊ​ትህ ይቆም ዘንድ አይ​ች​ልም።


በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ የሚ​ቋ​ቋ​ምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበ​ርሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፥ ቸልም አል​ል​ህም።


የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌ​ብም ሦስ​ቱን የዔ​ና​ቅን ልጆች ሱሲን፥ ተለ​ሚ​ንና አካ​ሚን ከዚያ አጠ​ፋ​ቸው።


አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ከፊ​ታ​ችሁ እስ​ኪ​ደ​መ​ሰሱ ድረስ ያጠ​ፋ​ላ​ች​ኋል፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም እነ​ር​ሱ​ንና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ የዱር አራ​ዊ​ትን ይሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።


ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሕ​ዛ​ብን ሁሉ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ችን አሳ​ደደ፤ ስለ​ዚህ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን ነውና እኛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን።”