ኢያሱ 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረችውም ምድር ይህች ናት፤ የፍልስጥኤማውያን፥ የጌሴርያውያንና የከነዓናውያን ሀገር ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሚቀረውም ምድር ይህ ነው፤ “እርሱም የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳይያዝ የቀረውም ምድር ይህ ነው፥ የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገና ያልተያዙትም እነዚህ ናቸው፦ የፍልስጥኤምና የገሹር ግዛት በሙሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረችውም ምድር ይህች ናት፥ የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ፥ |
በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ሌላ ራብ ሆነ፤ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቤሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።
እኔ አገልጋይህ በሶርያ ጌድሶር ሳለሁ፦ እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም ቢመልሰኝ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀርባለሁ ብዬ ስእለት ተስዬ ነበርና” አለው።
ሁለተኛውም ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቤግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌድሶር ንጉሥ ከቶልሜልም ልጅ ከመዓክ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ።
“ጢሮስና ሲዶና የፍልስጥኤም አውራጃ ገሊላም ሁሉ ሆይ! ከእናንተ ጋራ ምን አለኝ? እናንተ በቀልን ትበቀሉኛላችሁን? ቂምንስ ትቀየሙኛላችሁን? ፈጥኜ በችኰላ ፍዳን በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
በባሕር ዳር ለሚኖሩ ለከሊታውያን ሕዝብ ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብህም ሰው እንዳይኖር አጠፋሃለሁ።
የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌርጋሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህችንም የባሳንን ምድር እስከዚች ቀን ድረስ በስሙ አውታይ ኢያዕር ብሎ ጠራ።
የአርሞንኤምን ተራራ፥ ካሴኪን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌርጌሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ፤
ገለዓድንም፥ የጌሴሪያውያንንና የመከጢያውያንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳንንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥
የእስራኤል ልጆች ግን ጌሴሪያውያንን፥ መከጢያውያንንና ከነዓናውያንን አላጠፉአቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሴሪና መከጢ በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።
የከነዓናውያንንም ጦርነት ሁሉ ያላወቁትን እስራኤልን በእነርሱ ይፈትናቸው ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ተዋቸው።
ዳዊትና ሰዎቹም ወጥተው በጌሴራውያንና በአማሌቃውያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነዚህንም ቅጽር ባላቸው በጌላምሱርና በአኔቆንጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀምጠው አገኙአቸው።