Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ገለ​ዓ​ድ​ንም፥ የጌ​ሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ን​ንና የመ​ከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአ​ር​ሞ​ን​ዔ​ም​ንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በተጨማሪም ገለዓድን፣ የጌሹራውያንንና የማዕካታውያንን ግዛት ሁሉ፣ የአርሞንዔምን ተራራ በሙሉ፣ ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ ይይዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ገለዓድንም፥ የጌሹራውያንንና የማዕካታውያንን ግዛት ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እርሱም ገለዓድን፥ የገሹርንና የማዕካን አውራጃዎችና የአርሞንኤምን ተራራ በሙሉ እንዲሁም እስከ ሳለካ ድረስ ያለውን ባሳንን ይጨምራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ገለዓድንም፥ የጌሹራውያንንና የማዕካታውያንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 13:11
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤስ​ሮ​ምም ጌሱ​ር​ንና አራ​ምን የኢ​ያ​ዔ​ርን ከተ​ሞች ከቄ​ና​ትና ከመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ ጋር ስድ​ሳ​ውን ከተ​ሞች ወሰደ። እነ​ዚህ ሁሉ የገ​ለ​ዓድ አባት የማ​ኪር ልጆች ከተ​ሞች ነበሩ።


እን​ጀ​ራም ሊበሉ ተቀ​መጡ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ነሡ ጊዜ እነሆ፥ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ድ​ያን ከገ​ለ​ዓድ ሲመጡ አዩ፤ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ሽቱና በለ​ሳን፥ ከር​ቤም ተጭ​ነው ነበር። ወደ ግብፅ ሀገ​ርም ሊያ​ራ​ግፉ ይሄዱ ነበር።


ሙሴም፥ “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች ሁላ​ቸው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለጦ​ር​ነት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገሩ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ድል ብት​ነሡ ፥ የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።


የሚ​ሶ​ር​ንም ከተ​ሞች ሁሉ፥ የገ​ለ​ዓ​ድ​ንም ሁሉ፥ የባ​ሳ​ን​ንም ሁሉ እስከ ኤል​ከ​ድና እስከ ኤድ​ራ​ይን ድረስ በባ​ሳን የሚ​ኖር የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ከተ​ሞች ሁሉ ወሰ​ድን።


በም​ሥ​ራ​ቃዊ ባሕር ዳርቻ ወዳ​ለው ወደ ከነ​ዓ​ና​ዊው፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር ወዳ​ለው ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ በቆ​ላ​ማ​ውና በመ​ሴፋ ወዳ​ለው ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉም ላከ።


የቀ​ረ​ች​ውም ምድር ይህች ናት፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ የጌ​ሴ​ር​ያ​ው​ያ​ንና የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሀገር ሁሉ፥


በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገሠ የአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተ​ሞ​ችን ሁሉ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፥


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢያ​ዜ​ርና የገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ሁሉ፥ የአ​ሞ​ንም ልጆች ምድር እኩ​ሌታ በራ​ባት ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አሮ​ዔር ድረስ፥


ዕጣ​ቸ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ከአ​ለው ከገ​ለ​ዓ​ድና ከባ​ሳን ሀገር በቀር ለም​ናሴ ዐሥር ዕጣ ሆነ፤


የጋ​ድም ልጆች በባ​ሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ በአ​ፋ​ዛ​ዣ​ቸው ተቀ​መጡ።


ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግ​ረው ወደ ጋድና ወደ ገለ​ዓድ ምድር የሄዱ አሉ፤ ሳኦል ግን ገና በጌ​ል​ጌላ ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው እር​ሱን መከ​ተ​ልን ትተው ተበ​ተኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች