Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን ጌሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ንን፥ መከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ን​ንና ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሴ​ሪና መከጢ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ይኖ​ራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ነገር ግን እስራኤላውያን የጌሹርንና የማዕካትን ሕዝብ ስላላስወጡ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በመካከላቸው ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የእስራኤል ልጆች ግን ጌሹራውያንንና ማዕካታውያንን አላስወጡም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሹርና ማዕካት በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ይሁን እንጂ እስራኤላውያን የገሹርንና የማዕካን ሕዝብ አላስወጡም፤ ነገር ግን እነርሱ እስከ አሁን በእስራኤላውያን መካከል ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእስራኤል ልጆች ግን ጌሹራውያንንና ማዕካታውያንን አላወጡም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሹርና ማዕካት በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 13:13
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ገለ​ዓ​ድ​ንም፥ የጌ​ሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ን​ንና የመ​ከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአ​ር​ሞ​ን​ዔ​ም​ንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥


የሀ​ገ​ሩ​ንም ስዎች ከፊ​ታ​ችሁ ባታ​ሳ​ድዱ፥ ያስ​ቀ​ራ​ች​ኋ​ቸው ለዐ​ይ​ና​ችሁ እንደ እሾህ፥ ለጐ​ና​ች​ሁም እንደ አሜ​ከላ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ምድር ያስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ኋል።


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቤ​ግያ የተ​ወ​ለ​ደው ዶሎ​ሕያ ነበረ። ሦስ​ተ​ኛ​ውም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከቶ​ል​ሜ​ልም ልጅ ከመ​ዓክ የተ​ወ​ለ​ደው አቤ​ሴ​ሎም ነበረ።


የም​ናሴ ልጅ ኢያ​ዕር እስከ ጌር​ጋ​ሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአ​ር​ጎ​ብን አው​ራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ች​ንም የባ​ሳ​ንን ምድር እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ በስሙ አው​ታይ ኢያ​ዕር ብሎ ጠራ።


የአ​ር​ሞ​ን​ኤ​ምን ተራራ፥ ካሴ​ኪን፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ እስከ ጌር​ጌ​ሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገ​ለ​ዓ​ድ​ንም እኩ​ሌታ እስከ ሐሴ​ቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገ​ዛው የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ፤


በባ​ሳን የነ​በ​ረ​ውን፥ በአ​ስ​ታ​ሮ​ትና በኤ​ን​ድ​ራ​ይን የነ​ገ​ሠ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ሁሉ፤ እር​ሱም ከረ​ዓ​ይት የቀረ ነበረ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሙሴ አወ​ጣ​ቸው፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።


ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አል​ተ​ሰ​ጠም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስ​ታ​ቸው ነውና፥ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሞ​ዓብ ሜዳ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዳ​ካ​ፈ​ላ​ቸው እን​ዲሁ ተካ​ፈሉ።


ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወጥ​ተው በጌ​ሴ​ራ​ው​ያ​ንና በአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ቅጽር ባላ​ቸው በጌ​ላ​ም​ሱ​ርና በአ​ኔ​ቆ​ን​ጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀ​ም​ጠው አገ​ኙ​አ​ቸው።


የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤


የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ወገ​ኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአ​ሞን ልጆች ልከው ከቤ​ት​ሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያ​ንና ከሱባ ሶር​ያ​ው​ያን ሃያ ሺህ እግ​ረ​ኞ​ችን፥ ከአ​ማ​ሌቅ ንጉ​ሥም አንድ ሺህ ሰዎ​ችን፥ ከአ​ስ​ጦ​ብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ቀጠሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች