የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ንም ሁሉ ካደ​ረ​ገች በኋላ፦ ወደ እኔ ተመ​ለሽ አል​ኋት፤ ነገር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ አታ​ላይ እኅቷ ይሁ​ዳም አየች።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህን ሁሉ ካደረገች በኋላ፣ ወደ እኔ ትመለሳለች ብዬ ነበር፤ ሆኖም አልተመለሰችም፤ ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳም ይህን አየች።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

‘ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ ወደ እኔ ትመለሳለች’ ብዬ ነበር፤ ነገር ግን አልተመለሰችም፤ አታላይ እኅትዋም ይሁዳ አየች።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህን ሁሉ ከፈጸመች በኋላ እንደገና ወደ እኔ የምትመለስ መስሎኝ ነበር፤ እርስዋ ግን አልተመለሰችም፤ እምነት የማይጣልባት የእርስዋ እኅት ይሁዳም ይህን ሁሉ አይታለች።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ፦ ወደ እኔ ትመለሳለች ብዬ ነበር፥ ነገር ግን አልተመለሰችም፥ አታላይ እኅትዋም ይሁዳ አየች።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 3:7
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን የአ​ባ​ቱን አም​ላክ ፈለገ፤ በአ​ባ​ቱም ትእ​ዛዝ ሄደ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥራ አይ​ደ​ለም።


አቤቱ! ከአ​ንተ ጋር በተ​ም​ዋ​ገ​ትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ጋር ስለ ፍርድ ልና​ገር። የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች መን​ገድ ስለ ምን ይቀ​ናል? በደ​ል​ንስ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላ​ቸ​ዋል?


“ይህ ሕዝብ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ወገን ጥሎ​አ​ቸ​ዋል፥ እን​ዲሁ በፊ​ታ​ቸው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሕዝብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝ​ቤን አቃ​ል​ለ​ዋል ያለ​ውን ነገር አት​መ​ለ​ከ​ት​ምን?


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወን​ጅ​ለ​ዋል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ታላ​ቂ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በስተ ግራሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰማ​ርያ ናት፤ ታና​ሽ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰዶም ናት።


አንቺ ግን በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው አል​ሄ​ድ​ሽም፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም አላ​ደ​ረ​ግ​ሽም፤ ያው ለአ​ንቺ ጥቂት ነበ​ረና በመ​ን​ገ​ድሽ ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ የሚ​ከፋ ኀጢ​አት አደ​ረ​ግሽ።


ሕዝ​ቤም ከመ​ኖ​ሪ​ያው ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ብሩ ላይ ተቈጣ፤ ከፍ ከፍም አያ​ደ​ር​ገ​ውም።


ሰማ​ርያ በአ​ም​ላ​ክዋ ላይ ዐም​ፃ​ለ​ችና ፈጽማ ትጠ​ፋ​ለች፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል።


የሁ​ለት ወይም የሦ​ስት ከተ​ሞች ሰዎች ወደ አን​ዲት ከተማ ውኃ ይጠጡ ዘንድ ሄዱ፤ ነገር ግን አል​ረ​ኩም፤ እና​ንተ ግን ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።