የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላ​ሜን፥ ቸር​ነ​ቴ​ንና ምሕ​ረ​ቴን፥ ከዚህ ሕዝብ አስ​ወ​ግ​ጄ​አ​ለ​ሁና ልቅሶ ወዳ​ለ​በት ቤት አት​ግባ፤ ታለ​ቅ​ስና ታዝ​ንም ዘንድ አት​ሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “በረከቴን፣ ፍቅሬንና ምሕረቴን ከዚህ ሕዝብ አርቄአለሁና፤ ልቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ ታለቅስና ታዝንም ዘንድ አትሂድ” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰላሜን፥ ቸርነትንና ጽኑ ፍቅርን፥ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና ልቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፥ ለማልቀስም ሆነ ለማዘን አትሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ለቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ ስለ ማንም ሐዘንህን አትግለጥ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝቤን በሰላም አልባርክም፤ ዘላቂ ፍቅርና ምሕረትም አላሳያቸውም፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰላሜን፥ ቸርነትና ምሕረትን፥ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና ልቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፥ ታለቅስም ታዝንም ዘንድ አትሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 16:5
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እጆቼን በን​ጽ​ሕና አጥ​ባ​ለሁ፤ አቤቱ፥ መሠ​ዊ​ያ​ህን እዞ​ራ​ለሁ፥


ዘግ​ይቶ ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ልም​ላሜ ሁሉ አይ​ገ​ኝም፤ ከቲ​ኣሳ የም​ት​መጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕ​ዝቤ አል​ቅሱ፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝብ ነውና፤ ስለ​ዚህ ፈጣ​ሪው አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ሠሪ​ውም ምሕ​ረት አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም።


ወራ​ዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥ​ተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበ​ላ​ልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።


ሰው​ንና ወን​ድ​ሙን፥ አባ​ቶ​ች​ንና ልጆ​ችን በአ​ንድ ላይ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አላ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ም​ራ​ቸ​ው​ምም።”


ስለ​ዚህ ከዚች ምድር እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ አላ​ወ​ቃ​ች​ኋት ምድር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ምሕ​ረ​ትን ለማ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ ሌሎች አማ​ል​ክት ቀንና ሌሊት ታገ​ለ​ግ​ላ​ላ​ችሁ።”


ነፍ​ሴን ከሰ​ላም አራቀ፤ በጎ ነገ​ርን ረሳሁ።


ከዚያ ወራት አስቀድሞ ለሰውና ለእንስሳ ዋጋ አልነበረምና፣ እኔም ሰውን ሁሉ በወንድሙ ላይ አስነሥቼ ነበርና ከአስጨናቂው የተነሣ ለሚገባውና ለሚወጣው ሰላም አልነበረም።


በዚ​ያም ቀን ቍጣዬ ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እተ​ዋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መብል ይሆ​ናሉ፤ በዚ​ያም ቀን፦ በእ​ው​ነት አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ና​ልና፥ በእ​ኛም መካ​ከል የለ​ምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገ​ኘን እስ​ኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት ይደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋል።


ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፤ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።