የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልጅ​ህን ከእኔ ያር​ቀ​ዋ​ልና፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ያመ​ል​ካ​ልና። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፤ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ች​ኋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምክንያቱም እኔን ከመከተል ልጆችህን መልሰው ሌሎችን አማልክት እንዲያመልኩ ስለሚያደርጉና ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ቍጣ በላይህ ነድዶ፣ ፈጥኖ ስለሚያጠፋህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔን እንዳይከተል፥ ሌሎችንም አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና፤ ያኔ የጌታ ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ፈጥኖም ያጠፋችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህን ብታደርግ ልጆችህን ከእግዚአብሔር አስኰብልለው ባዕዳን አማልክትን እንዲከተሉ ያደርጉአቸዋል፤ ይህም ከሆነ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ተቈጥቶ ወዲያው ያጠፋሃል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዳይከተለኝ ሌሎችንም አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ፈጥኖም ያጠፋችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 7:4
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት መሄድ አል​በ​ቃ​ውም፤ የሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ን​ንም ንጉሥ የኤ​ያ​ት​ባ​ሔ​ልን ልጅ ኤል​ዛ​ቤ​ልን አገባ፤ ሄዶም በዓ​ልን አመ​ለከ ሰገ​ደ​ለ​ትም።


አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና። በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤


ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ም​ንም ከወ​ንድ ልጆ​ችህ፥ ሴቶች ልጆ​ች​ህ​ንም ከወ​ንድ ልጆ​ቻ​ቸው ጋር እን​ዳ​ታ​ጋባ፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው ሲያ​መ​ነ​ዝሩ ከአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በኋላ ሄደው አመ​ን​ዝ​ረ​ውም ልጆ​ች​ህን እን​ዳ​ያ​ስቱ ተጠ​ን​ቀቅ።


ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው ያደ​ረ​ጉ​ትን ርኵ​ሰት ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ችሁ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት እን​ዳ​ት​ሠሩ ትረ​ግ​ማ​ቸ​ዋ​ለህ።


ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ከም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ድ​ት​ጠፉ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በእ​ና​ንተ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ፈጽ​ሞም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም።


በመ​ካ​ከ​ልህ ያለው አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀና​ተኛ አም​ላክ ነውና የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቁጣ እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድ​ብህ፥ ከም​ድ​ርም ፊት እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋህ ተጠ​ን​ቀቅ።


በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ደረሱ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው


እና​ንተ ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ብት​ጠጉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ብት​ጋቡ፥ እና​ን​ተም ወደ እነ​ርሱ፥ እነ​ር​ሱም ወደ እና​ንተ ብት​ደ​ራ​ረሱ፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ በዓ​ሊ​ም​ንም አመ​ለኩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህ ሕዝብ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ያዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ስለ ተላ​ለፉ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥


ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም አገ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው ሰጡ፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አመ​ለኩ።