Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -

ዘዳግም 20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ስለ ጦር​ነት የተ​ሰጡ መመ​ሪ​ያ​ዎች

1 “ጠላ​ቶ​ች​ህን ለመ​ው​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሕዝ​ቡ​ንም ከአ​ንተ ይልቅ በዝ​ተው ባየህ ጊዜ፥ ከግ​ብፅ ሀገር ያወ​ጣህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍ​ራ​ቸው።

2 ወደ ጦር​ነ​ትም በቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ ካህኑ ይቅ​ረብ፤ ለሕ​ዝ​ቡም እን​ዲህ ብሎ ይን​ገ​ራ​ቸው፦

3 እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ ዛሬ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ለመ​ው​ጋት ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ልባ​ችሁ አይ​ታ​ወክ፤ አት​ፍሩ፤ አት​ሸ​በሩ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም ፈቀቅ አት​በሉ፤

4 ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄድ፥ ያድ​ና​ች​ሁም ዘንድ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ስለ እና​ንተ የሚ​ወጋ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።

5 ጸሐ​ፍ​ትም ለሕ​ዝቡ እን​ዲህ ብለው ይና​ገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላ​ስ​መ​ረቀ ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ስ​መ​ር​ቀው ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።

6 ወይ​ንም ተክሎ ደስ ያል​ተ​ሰ​ኘ​በት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው ደስ እን​ዳ​ይ​ሰ​ኝ​በት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።

7 ሚስ​ትም አጭቶ ያላ​ገ​ባት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ገ​ባት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።

8 ጸሐ​ፍ​ቱም ደግሞ ጨም​ረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድን​ጉጥ ሰው ቢሆን የወ​ን​ድ​ሞ​ቹን ልብ እንደ እርሱ እን​ዳ​ያ​ስ​ፈራ ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ ብለው ለሕ​ዝቡ ይና​ገሩ።

9 ጸሐ​ፍ​ቱም ለሕ​ዝቡ ነግ​ረው በጨ​ረሱ ጊዜ ከታ​ላ​ላቁ ሕዝብ መካ​ከል የሠ​ራ​ዊት አለ​ቆ​ችን ይሹሙ።

10 “ለመ​ዋ​ጋት ወደ አን​ዲት ከተማ በደ​ረ​ስህ ጊዜ አስ​ቀ​ድ​መህ በሰ​ላም ቃል ጥራ​ቸው።

11 የሰ​ላም ቃልም ቢመ​ል​ሱ​ልህ ደጅም ቢከ​ፍ​ቱ​ልህ፥ በከ​ተ​ማው ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገ​ብ​ሩ​ልህ፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ይሁ​ኑህ።

12 የሰ​ላም ቃልም ባይ​መ​ል​ሱ​ልህ ከአ​ን​ተም ጋር መዋ​ጋት ቢወ​ድዱ፥ አንተ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ትከ​ብ​ባ​ለህ፤

13 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣት ጊዜ፥ በእ​ር​ስዋ ያሉ​ትን ወን​ዶች ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት ትገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤

14 ከሴ​ቶ​ቹና ከጓዙ በቀር እን​ስ​ሶ​ቹን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ያለ​ውን ምርኮ ሁሉ ዘር​ፈህ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የጠ​ላ​ቶ​ች​ህን ምርኮ ትበ​ላ​ለህ።

15 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ርስ ዘንድ ምድ​ራ​ቸ​ውን ከሚ​ሰ​ጥህ ከእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ከተ​ሞች ባይ​ደ​ሉት ከአ​ንተ እጅግ በራ​ቁት ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ ታደ​ር​ጋ​ለህ።

16 ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም ነፍስ አታ​ድ​ንም።

17 ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘህ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ዉን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ዉን፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ዉ​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ዉ​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉ​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉ​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉ​ንም ፈጽ​መህ ትረ​ግ​ማ​ቸ​ዋ​ለህ።

18 ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው ያደ​ረ​ጉ​ትን ርኵ​ሰት ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ችሁ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት እን​ዳ​ት​ሠሩ ትረ​ግ​ማ​ቸ​ዋ​ለህ።

19 “ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​ው​ጋ​ትና ለመ​ው​ሰድ ብዙ ቀን ብት​ከ​ብ​ባት፥ ምሳ​ር​ህን አን​ሥ​ተህ ዛፎ​ች​ዋን አት​ቍ​ረጥ፤ ከእ​ነ​ርሱ ትበ​ላ​ለ​ህና አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው፤ ወደ አንተ ይመ​ጣና ወደ ቅጥ​ር​ህም ይገባ ዘንድ የም​ድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን?

20 ለመ​ብል የማ​ይ​ሆ​ኑ​ትን የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ዛፎች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ትቈ​ር​ጣ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ እስ​ክ​ታ​ሸ​ን​ፋ​ትም ድረስ በም​ት​ዋ​ጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመ​ሽ​ጋ​ለህ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች