የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ቈላስይስ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የተ​ሰ​ወረ የጥ​በ​ብና የም​ክር መዝ​ገብ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የተሰወረ የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የሚገኘው በርሱ ዘንድ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጥበብና የእውቀት ሀብት ሁሉ ተሰውሮ የሚገኘው በክርስቶስ ዘንድ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የጥበብና የዕውቀት ሀብት ተሰውሮ የሚገኘው በክርስቶስ ዘንድ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት



ቈላስይስ 2:3
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም የፈ​ረ​ደ​ውን ፍርድ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍር​ድን ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በእ​ርሱ ላይ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከን​ጉሡ ፊት የተ​ነሣ ፈሩ።


በሰው ሁሉ ዘንድ ተረ​ስ​ታ​ለች፥ ከሰ​ማይ ወፎ​ችም ተሰ​ው​ራ​ለች።


እርስዋንም እንደ ብር ብትፈልጋት፥ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ፥ የጥ​በ​ብና የማ​ስ​ተ​ዋል መን​ፈስ፥ የም​ክ​ርና የኀ​ይል መን​ፈስ፥ የዕ​ው​ቀ​ትና የእ​ው​ነት መን​ፈስ ያር​ፍ​በ​ታል።


ወይስ ከማን ጋር ተመ​ካ​ከረ? ወይስ ማን መከ​ረው? ፍር​ድ​ንስ ማን አስ​ተ​ማ​ረው? የጥ​በ​ብ​ንስ መን​ገድ ማን አሳ​የው?


“እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።


ስለ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበቡ እን​ዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢ​ያ​ት​ንና ሐዋ​ር​ያ​ትን ወደ እነ​ርሱ እል​ካ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ይገ​ድ​ላሉ፤ ያሳ​ድ​ዳ​ሉም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጠ​ግ​ነት፥ ጥበ​ብና ዕው​ቀት እን​ዴት ጥልቅ ነው! ለመ​ን​ገ​ዱም ፍለጋ የለ​ውም፤ ፍር​ዱ​ንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም።


ለእኛ ለዳ​ን​ነው ግን ከአ​ይ​ሁድ፥ ከአ​ረ​ሚም ብን​ሆን ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጥበብ ነው።


እና​ን​ተም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ርሱ ናችሁ፤ በእ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ጽድ​ቅን፥ ቅድ​ስ​ና​ንና ቤዛ​ነ​ትን አገ​ኘን።


ይኸ​ውም በፍ​ጹም ጥበ​ብና ምክር ለእኛ አብ​ዝቶ ያደ​ረ​ገው ነው።


ሁሉ በእ​ርሱ ፍጹም ሆኖ ይኖር ዘንድ፥ ወዶ​አ​ልና።


እር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ፍጹም የሚ​ሆ​ነ​ውን ሰው እና​ቀ​ር​በው ዘንድ፥ እኛ የም​ና​ስ​ተ​ም​ር​ለት፥ ሰውን ሁሉ ወደ እርሱ የም​ን​ጠ​ራ​ለ​ትና የም​ን​ገ​ሥ​ጽ​ለት፥ ሥራ​ው​ንም በጥ​በብ ሁሉ የም​ን​ና​ገ​ር​ለት ነው።


ስለ​ዚ​ህም እኛ ዜና​ች​ሁን ከሰ​ማን ጀምሮ፥ በፍ​ጹም ጥበ​ብና በፍ​ጹም መን​ፈ​ሳዊ ምክር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ ማወ​ቅን ትፈ​ጽሙ ዘንድ፥ ስለ እና​ንተ መጸ​ለ​ይ​ንና መለ​መ​ንን አል​ተ​ው​ንም።


በጥ​በብ ሁሉ እን​ድ​ት​በ​ለ​ጽጉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ና​ንተ ዘንድ ይጽና፤ በመ​ን​ፈ​ስም ራሳ​ች​ሁን አስ​ተ​ምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የቅ​ድ​ስና ማሕ​ሌ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ በጸጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ።


እና​ንተ ፈጽ​ማ​ችሁ ሞታ​ች​ኋ​ልና፤ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ሠ​ወ​ረች ናትና።


ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።