Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ቈላስይስ 2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ስለ እና​ንተ እና በሎ​ዶ​ቅያ ስላሉ፥ ፊቴ​ንም በሥጋ ስላ​ላ​ዩት ምእ​መ​ናን ሁሉ ምን ያህል እን​ደ​ም​ጋ​ደል ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ።

2 ይኸ​ውም ልቡ​ና​ቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትም​ህ​ር​ታ​ቸ​ውም በማ​ወቅ፥ በፍ​ቅ​ርና ፍጹ​ም​ነት ባለው ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በጥ​በ​ብና በሃ​ይ​ማ​ኖት፥ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም የሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር በማ​ወቅ ይጸና ዘንድ ነው።

3 የተ​ሰ​ወረ የጥ​በ​ብና የም​ክር መዝ​ገብ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ አለ።

4 ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ በሚ​ያ​ባ​ብል ነገር የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ነው።

5 እኔ በሥጋ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባል​ኖ​ርም እን​ኳን፥ በመ​ን​ፈስ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባ​ያ​ች​ሁ​ንና ሥር​ዐ​ታ​ች​ሁን፥ በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያለ የእ​ም​ነ​ታ​ች​ሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለ​ኛል።

6 እን​ግ​ዲህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እንደ ተቀ​በ​ላ​ች​ሁት፥ በእ​ርሱ ተመ​ላ​ለሱ።

7 በእ​ርሱ ተመ​ሥ​ር​ታ​ችሁ ታነጹ፤ በም​ስ​ጋ​ናው ትበዙ ዘንድ፥ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሃይ​ማ​ኖት ጽኑ።

8 ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ።

9 በእ​ርሱ ፍጹም መለ​ኮቱ በሥጋ ተገ​ልጦ ይኖ​ራ​ልና።

10 እና​ን​ተም በእ​ርሱ ፍጹ​ማን ሁኑ፤ እርሱ ለአ​ለ​ቅ​ነት ሁሉና ለሥ​ል​ጣን ሁሉ ራስ ነውና።

11 የኀ​ጢ​አ​ትን ሰው​ነት ሸለ​ፈት በመ​ግ​ፈፍ በክ​ር​ስ​ቶስ መገ​ረዝ በሰው እጅ የአ​ል​ተ​ደ​ረገ መገ​ረ​ዝን በእ​ርሱ ሆና​ችሁ ተገ​ረ​ዛ​ችሁ።

12 በጥ​ም​ቀ​ትም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሙ​ታን ለይቶ ባስ​ነ​ሣው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ት​ነ​ትና በሃ​ይ​ማ​ኖት ከእ​ርሱ ጋር ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል።

13 እና​ን​ተም በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁና ሥጋ​ች​ሁን ባለ​መ​ገ​ረዝ ሙታን ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ከእ​ርሱ ጋር ሕያ​ዋን አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ይቅር አላ​ችሁ።

14 ከባ​ላ​ጋ​ራ​ችን የተ​ነሣ በት​እ​ዛዝ የተ​ጻ​ፈ​ውን የዕ​ዳ​ች​ንን ደብ​ዳቤ ደመ​ሰ​ሰ​ልን፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም አራ​ቀው፤ በመ​ስ​ቀ​ሉም ቸነ​ከ​ረው።

15 አለ​ቆ​ች​ንና ገዢ​ዎ​ችን በመ​ግ​ፈፉ በግ​ልጥ አሳ​ያ​ቸው፤ ራቁ​ቱን በመ​ሆ​ኑም አሳ​ፈ​ራ​ቸው።

16 እን​ግ​ዲህ በመ​ብ​ልም ቢሆን፥ በመ​ጠ​ጥም ቢሆን፥ በልዩ ልዩ በዓ​ላ​ትም ቢሆን፥ በመ​ባ​ቻም ቢሆን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቢሆን የሚ​ነ​ቅ​ፋ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ።

17 ይህ ሁሉ ይመጣ ዘንድ ላለው ጥላ ነውና። አካሉ ግን የክ​ር​ስ​ቶስ ነው።

18 በመ​ታ​ለ​ልና ራስን ዝቅ በማ​ድ​ረግ ለመ​ላ​እ​ክት አም​ልኮ ትታ​ዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአ​ላ​የ​ውም በከ​ንቱ የሥ​ጋው ምክር እየ​ተ​መካ የሚ​ያ​ሰ​ን​ፋ​ችሁ አይ​ኑር።

19 ሥጋ ሁሉ ጸንቶ በሚ​ኖ​ር​በት፥ በሥ​ርና በጅ​ማ​ትም በሚ​ስ​ማ​ማ​በት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሚ​ያ​ድ​ግ​በ​ትና በሚ​ጸ​ና​በት፥ በሚ​ሞ​ላ​በ​ትም በራስ አይ​ጸ​ናም።


አዲስ ሕይ​ወት በክ​ር​ስ​ቶስ

20 ከዚህ ዓለም ኑሮ ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ታ​ችሁ እን​ደ​ገና በዓ​ለም እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች እን​ዴት ትሠ​ራ​ላ​ችሁ?

21 እን​ዴ​ትስ ይህን አት​ዳ​ስስ፥ ይህን አት​ንካ፥ ይህ​ንም አት​ቅ​መስ ይሉ​አ​ች​ኋል?

22 ይህ ሁሉ እንደ ሰው ትእ​ዛ​ዝና ትም​ህ​ርት ለጥ​ፋት ነውና።

23 ይህም ስለ ልብ ትሕ​ት​ናና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስለ መፍ​ራት፥ ለሥጋ ስለ አለ​ማ​ዘን ጥበ​ብን ይመ​ስ​ላል፤ ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለ​ውም።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች