የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ንጉሡ በቤቱ በተ​ቀ​መጠ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዙ​ሪ​ያው ያሉ ጠላ​ቶ​ቹን ሁሉ ባወ​ረ​ሰው ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡ በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ ከተቀመጠና እግዚአብሔርም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ካሳረፈው በኋላ፣

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ንጉሡ በቤተ መንግሥቱ ከተቀመጠና ጌታም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ካሳረፈው በኋላ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉ ስለ ጠበቀው ንጉሥ ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በሰላም ይኖር ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም ሆነ፥ ንጉሡ በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ እግዚአብሔርም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ባሳረፈው ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 7:1
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም፥ ድን​ጋይ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም ላከ፤ ለዳ​ዊ​ትም ቤት ሠሩ​ለት።


የሳ​ኦ​ልም ልጅ ሜል​ኮል እስከ ሞተ​ች​በት ቀን ድረስ ልጅ አል​ወ​ለ​ደ​ችም።


በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆ​ችን በሾ​ምሁ ጊዜ ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ሁሉ አሳ​ር​ፍ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ፦ ቤት እን​ደ​ም​ት​ሠ​ራ​ለት ይነ​ግ​ር​ሃል፤ እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና።


አሁ​ንም አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ሪ​ያዬ ካሉት ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ክፉም ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ጠላት የለ​ብ​ኝም።


ልጁ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን ጠርቶ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ይሠራ ዘንድ አዘ​ዘው።


ዳዊ​ትም ሰሎ​ሞ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ በልቤ አስቤ ነበር።


ንጉ​ሡም ዳዊት በጉ​ባ​ኤው መካ​ከል ቆሞ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦ​ትና ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እግር ማረ​ፊያ የዕ​ረ​ፍት ቤት ለመ​ሥ​ራት አሳብ በልቤ መጣ​ብኝ፤ ለዚ​ህም ሥራ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤


በይ​ሁ​ዳም ምሽ​ጎች ከተ​ሞ​ችን ሠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕረ​ፍት ስለ ሰጠው ምድ​ሪቱ ጸጥ ብላ ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን ጦር​ነት አል​ነ​በ​ረም።


የኢ​ዮ​ሣ​ፍ​ጥም መን​ግ​ሥት ሰላም ሆነች፤ አም​ላ​ኩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ሪ​ያው ካሉ አሳ​ረ​ፈው።


ሰማ​ያት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ይና​ገ​ራሉ፥ የሰ​ማ​ይም ጠፈር የእ​ጁን ሥራ ያወ​ራል።


ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።


አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት፤ ሌላም አምስት አተረፈ፤


ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባለ​መ​ዋ​ል​ነ​ትን አግ​ኝቶ ለያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ማደ​ሪያ ያገኝ ዘንድ ለመነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ማለ​ላ​ቸው በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት አሳ​ረ​ፋ​ቸው፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ይቋ​ቋ​ማ​ቸው ዘንድ ማንም ሰው አል​ቻ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ካሳ​ረፈ በኋላ፥ ኢያሱ ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም ዐለፈ፤