የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ በዳ​ዊት አገ​ል​ጋ​ዮች ፊት ወደቁ፤ በዚ​ያም ቀን ታላቅ ውጊያ በዚያ ሆነ፤ ሃያ ሺህ ሰዎ​ችም ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እዚያም የእስራኤል ሰራዊት በዳዊት ሰዎች ተመታ፤ በዚያም ቀን ታላቅ ዕልቂት ሆነ፤ ሃያ ሺሕም ሰው ተገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እዚያም የእስራኤል ሠራዊት በዳዊት አገልጋዮች ተመታ፤ በዚያም ቀን ታላቅ እልቂት ሆነ፤ ሃያ ሺህም ሰዎችም ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያንም በዳዊት ተከታዮች ድል ተመቱ፤ በዚያን ቀን የሞቱባቸው ሰዎች ቊጥር ኻያ ሺህ ያኽል ስለ ነበር የሽንፈታቸው ሁኔታ እጅግ አሠቃቂ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም የእስራኤል ሕዝብ በዳዊት ባሪያዎች ፊት ተመቱ፥ በዚያም ቀን ታላቅ ውጊያ በዚያ ሆነ፥ ሀያ ሺህ ሰውም ሞተ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 18:7
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በን​ጉሡ ዘንድ ሊፋ​ረዱ ለሚ​መጡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ አቤ​ሴ​ሎም እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ልብ ማረከ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ወደ በረሓ ወጡ፤ በኤ​ፍ​ሬ​ምም በረሓ ተዋ​ጓ​ቸው።


ከዚ​ያም ጦሩ በሀ​ገሩ ሁሉ ፊት ተበ​ተነ፤ በዚ​ያም ቀን በሰ​ይፍ ከተ​ገ​ደ​ሉት ሕዝብ ይልቅ በበ​ረሓ የሞቱ ይበ​ዛሉ።


በዚ​ያም ቀን እጅግ ጽኑ ሰልፍ ሆነ፤ በዳ​ዊ​ትም ሰዎች ፊት አበ​ኔ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ተሸ​ነፉ።


አበ​ኔ​ርም ኢዮ​አ​ብን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ሰይፍ ለድል የም​ታ​ጠፋ አይ​ደ​ለ​ምን? ፍጻ​ሜ​ዋስ መራራ እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምን? ሕዝቡ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ከማ​ሳ​ደድ ይመ​ለሱ ዘንድ ሕዝ​ቡን የማ​ት​ና​ገር እስከ መቼ ነው?”


የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ከብ​ን​ያም እና ከአ​በ​ኔር ሰዎች ሦስት መቶ ስድሳ ሰዎ​ችን ገደሉ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ነበ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በአ​ንድ ቀን ከይ​ሁዳ ጽኑ​ዓን የነ​በሩ መቶ ሃያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞ​ችን ገደለ፤


አቤቱ፥ ፍጥ​ረ​ትህ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ ጻድ​ቃ​ን​ህም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።


በሐሰት እጅን በእጅ የሚመታ አይድንም፤ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋን ያገኛል።


ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ ከእነርሱ ለአንዱ ስንኳ እንቢ አትበል።