Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 18:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እዚያም የእስራኤል ሰራዊት በዳዊት ሰዎች ተመታ፤ በዚያም ቀን ታላቅ ዕልቂት ሆነ፤ ሃያ ሺሕም ሰው ተገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እዚያም የእስራኤል ሠራዊት በዳዊት አገልጋዮች ተመታ፤ በዚያም ቀን ታላቅ እልቂት ሆነ፤ ሃያ ሺህም ሰዎችም ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እስራኤላውያንም በዳዊት ተከታዮች ድል ተመቱ፤ በዚያን ቀን የሞቱባቸው ሰዎች ቊጥር ኻያ ሺህ ያኽል ስለ ነበር የሽንፈታቸው ሁኔታ እጅግ አሠቃቂ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ በዳ​ዊት አገ​ል​ጋ​ዮች ፊት ወደቁ፤ በዚ​ያም ቀን ታላቅ ውጊያ በዚያ ሆነ፤ ሃያ ሺህ ሰዎ​ችም ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በዚያም የእስራኤል ሕዝብ በዳዊት ባሪያዎች ፊት ተመቱ፥ በዚያም ቀን ታላቅ ውጊያ በዚያ ሆነ፥ ሀያ ሺህ ሰውም ሞተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 18:7
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤሴሎም ፍትሕ ለማግኘት ወደ ንጉሡ የሚመጣውን እስራኤላዊ ሁሉ የሚቀርበው በዚህ መንገድ ስለ ነበር፣ የእስራኤልን ሰዎች ልብ ሰረቀ።


ሰራዊቱ እስራኤልን ለመውጋት ተሰልፎ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ጦርነቱም በኤፍሬም ደን ውስጥ ሆነ።


ውጊያው በገጠሩ ሁሉ ተስፋፋ፤ በዚያ ቀን ሰይፍ ከጨረሰው ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረው ሰው በለጠ።


የዚያን ዕለቱ ጦርነት እጅግ ከባድ ነበር፤ አበኔርና የእስራኤል ሰዎች በዳዊት ሰዎች ድል ሆኑ።


አበኔር ኢዮአብን ጠርቶ፣ “ይህ ሰይፍ ዘላለም ማጥፋት አለበትን? ውጤቱ መራራ መሆኑን አንተስ ሳታውቀው ቀርተህ ነውን? ሰዎችህ ወንድሞቻቸውን ማሳደዱን እንዲያቆሙ ትእዛዝ የማትሰጣቸውስ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አለው።


የዳዊት ሰዎች ግን ከአበኔር ጋራ ከነበሩት ሦስት መቶ ስድሳ ብንያማውያን ገደሉ።


ይሁዳ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለ ተወ፣ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ መቶ ሃያ ሺሕ ወታደሮች ገደለ።


ነገሥታትን ድል የሚያጐናጽፍ፣ ባሪያውን ዳዊትን ከሚጐዳ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።


ክፉ ሳይቀጣ እንደማይቀር ዕወቅ፣ ጻድቃን ግን በነጻ ይሄዳሉ።


ልጄ ሆይ፤ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፤ ከዐመፀኞችም ጋራ አትተባበር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች