Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 2:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 አበ​ኔ​ርም ኢዮ​አ​ብን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ሰይፍ ለድል የም​ታ​ጠፋ አይ​ደ​ለ​ምን? ፍጻ​ሜ​ዋስ መራራ እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምን? ሕዝቡ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ከማ​ሳ​ደድ ይመ​ለሱ ዘንድ ሕዝ​ቡን የማ​ት​ና​ገር እስከ መቼ ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አበኔር ኢዮአብን ጠርቶ፣ “ይህ ሰይፍ ዘላለም ማጥፋት አለበትን? ውጤቱ መራራ መሆኑን አንተስ ሳታውቀው ቀርተህ ነውን? ሰዎችህ ወንድሞቻቸውን ማሳደዱን እንዲያቆሙ ትእዛዝ የማትሰጣቸውስ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 አበኔር ኢዮአብን ጠርቶ፥ “ሰይፍ በውኑ እስከ ዘለዓለም ያጠፋልን? ፍጻሜውሳ መራራ እንደሆነ አታውቅምን? ሰዎችህ ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንዲገቱ ትእዛዝ የማትሰጣቸውስ እስከ መቼ ነው?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 አበኔርም፥ ኢዮአብን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ዘለዓለም ስንዋጋ እንኖራለንን? ፍጻሜውስ መራር መሆኑን አትገነዘብምን? ሰዎችህ እኛን ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንዲገቱ ትእዛዝ የማትሰጣቸው እስከ መቼ ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 አበኔርም ወደ ኢዮአብ ጮኸ፦ ሰይፍ በውኑ እስከ ዘላለም ያጠፋልን? ፍጻሜውሳ መራራ እንደ ሆነ አታውቅምን? ሕዝቡ ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ ይመለሱ ዘንድ ሕዝቡን የማትናገር እስከ መቼ ነው? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 2:26
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን፥ “ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፥ አንድ ጊዜም ያን ይበ​ላ​ልና ይህ ነገር በዐ​ይ​ንህ አይ​ክፋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ወ​ጉ​ትን አበ​ርታ፤ አፍ​ር​ሳ​ትም ብለህ ለኢ​ዮ​አብ ንገ​ረው፤ አን​ተም አጽ​ናው” አለው።


አበ​ኔ​ርም ኢዮ​አ​ብን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ችን ይነሡ፤ በፊ​ታ​ች​ንም ይቈ​ራ​ቈሱ” አለው፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “ይነሡ” አለ።


ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ የወ​ደ​ረ​ኛ​ውን ራስ በእጁ ያዘ፤ ሰይ​ፉ​ንም በወ​ደ​ረ​ኛው ጐን ሻጠ፤ ተያ​ይ​ዘ​ውም ወደቁ። የዚ​ያም ስፍራ ስም “በገ​ባ​ዖን የሸ​መቁ ሰዎች ድርሻ” ተብሎ ተጠራ፤


በአ​በ​ኔር ኋላ የነ​በሩ የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ተሰ​በ​ሰቡ፥ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሆኑ፤ በአ​ንድ ኮረ​ብ​ታም ራስ ላይ ቆሙ።


ኢዮ​አ​ብም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ባት​ና​ገር ኖሮ ሕዝቡ ሁሉ በጥ​ዋት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ በወጡ ነበር” አለ።


“ዝም የማ​ት​ለው እስከ መቼ ነው? እኛም እን​ድ​ን​ነ​ግ​ርህ ታገሥ።


“ነፍ​ሴን የም​ት​ነ​ዘ​ን​ዙ​አት፥ በቃ​ላ​ች​ሁስ የም​ታ​ደ​ቅ​ቁኝ እስከ መቼ ነው? ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ብኝ ዕወቁ፤


እና​ንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባ​ች​ሁን ታከ​ብ​ዳ​ላ​ችሁ? ከንቱ ነገ​ርን ለምን ትወ​ድ​ዳ​ላ​ችሁ? ሐሰ​ት​ንም ለምን ትሻ​ላ​ችሁ?


የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።


እንቢ ብት​ሉና ባት​ሰ​ሙኝ ግን ሰይፍ ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ወራ​ዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥ​ተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበ​ላ​ልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።


ልጆ​ቻ​ች​ሁን በከ​ንቱ ቀሥ​ፌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተግ​ሣ​ጼን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁም፤ ሰይ​ፋ​ችሁ እን​ደ​ሚ​ሰ​ብር አን​በሳ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በል​ቶ​አል፤ በዚ​ህም አል​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝም።


የሚ​ሸ​ሹ​ትን የም​መ​ለ​ከት፥ የመ​ለ​ከ​ቱ​ንስ ድምፅ የም​ሰማ እስከ መቼ ነው?


ያ ቀን ጠላ​ቶ​ቹን የሚ​በ​ቀ​ል​በት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የበ​ቀል ቀን ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በልቶ ይጠ​ግ​ባል፤ በደ​ማ​ቸ​ውም ይሰ​ክ​ራል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በሰ​ሜን ምድር በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ ነውና።


“በግ​ብፅ ተና​ገሩ፤ በሚ​ግ​ዶ​ልም አውሩ፤ በሜ​ም​ፎ​ስና በጣ​ፍ​ናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙ​ሪ​ያህ ያለ​ውን በል​ቶ​አ​ልና፦ ተነሥ ተዘ​ጋ​ጅም በሉ።


ጦር በከ​ተ​ማው ደከ​መች፤ ከእ​ጁም ይለ​ያ​ታል፤ ከሥ​ራ​ቸ​ውም ፍሬ ይበ​ላሉ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ሲጣሉ አገኘ፤ ሊያ​ስ​ታ​ር​ቃ​ቸ​ውም ወድዶ፦ ‘እና​ን​ተማ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ናችሁ፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ለምን ትጣ​ላ​ላ​ችሁ?’ አላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች