Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በን​ጉሡ ዘንድ ሊፋ​ረዱ ለሚ​መጡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ አቤ​ሴ​ሎም እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ልብ ማረከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አቤሴሎም ፍትሕ ለማግኘት ወደ ንጉሡ የሚመጣውን እስራኤላዊ ሁሉ የሚቀርበው በዚህ መንገድ ስለ ነበር፣ የእስራኤልን ሰዎች ልብ ሰረቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አቤሴሎም ፍርድ ለማግኘት ወደ ንጉሡ ለሚመጣ እስራኤላዊ ሁሉ አቀራረቡ እንዲህ ነበር፤ ስለዚህ አቤሴሎም የእስራኤልን ሰዎች ልብ ሰረቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አቤሴሎም ፍርድ ለማግኘት ወደ ንጉሡ ለሚመጡት ሁሉ እንደዚህ ያደርግ ስለ ነበር የእነርሱን ልብ ለመማረክ ቻለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እንዲሁም አቤሴሎም ከንጉሥ ፍርድ ሊሰማ ከእስራኤል ዘንድ በሚመጣ ሁሉ ያደርግ ነበር፥ አቤሴሎምም የእስራኤልን ሰዎች ልብ ሰረቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 15:6
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ልብ ወደ አቤ​ሴ​ሎም ተመ​ል​ሶ​አል የሚል መል​እ​ክ​ተኛ ወደ ዳዊት ሄደ።


በክፉዎች አፍ የሀገር ወጥመድ አለ፥ የጻድቃን ዕውቀት ግን መልካም ጎዳና ናት።


ከፀ​ሓይ በታች የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሕያ​ዋን ሁሉ በእ​ርሱ ፋንታ ከሚ​ነ​ሣው ከሌ​ላው ጐል​ማሳ ጋር ሆነው አየሁ።


እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤


ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም፤ ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች