2 ሳሙኤል 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ከተማዪቱን በከበበ ጊዜ ጀግኖች እንዳሉበት በሚያውቀው ስፍራ ኦርዮን አቆመው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ኢዮአብ ከተማዪቱን በከበባት ጊዜ፣ እጅግ ጠንካራ ተከላካዮች እንዳሉበት በሚያውቀው ግንባር ኦርዮን መደበው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ኢዮአብ ከተማዪቱን በከበባት ጊዜ፥ እጅግ ጠንካራ ተከላካዮች እንዳሉበት በሚያውቀው ግንባር ኦርዮንን መደበው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ኢዮአብ ከተማይቱን ከቦ በመያዝ ላይ ሳለ ጠላት ማየሉን በሚያውቅበት ስፍራ ኦርዮን አሰለፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ከተማይቱን በከበበ ጊዜ ጀግኖች እንዳሉበት በሚያውቀው ስፍራ ኦርዮን አቆመው። |
የከተማዪቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳዊትም አገልጋዮች ከሕዝቡ አንዳንዱ ወደቁ፤ ኬጤያዊው ኦርዮም ደግሞ ሞተ።
የኔር ልጅ የይሩበዓልን ልጅ አቤሜሌክን ማን ገደለው? አንዲት ሴት ከቅጥር ላይ የወፍጮ መጅ ጥላበት የሞተ አይደለምን? ስለምን ወደ ቅጥሩ እንደዚህ ቀረባችሁ? አንተም፦ ባሪያህ ኬጤያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።”
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቈይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፤ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ወገቡን መታው፤ ሞተም።
አንተም ደግሞ የሶርህያ ልጅ ኢዮአብ፥ ሁለቱን የእስራኤል ሠራዊት አለቆች የኔር ልጅ አበኔርን የኢያቴርንም ልጅ አሜሳይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደረገውን ታውቃለህ፤ የጦርነትንም ደም በሰላም አፈሰሰ፤ በወገቡም ባለው ድግና በእግሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።
ከዚህም በኋላ ኢዩ፥ “ወገኖቼስ ከሆናችሁ፥ ነገሬንም ከሰማችሁ የጌታችሁን ልጆች ራስ ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይዝራኤል ወደ እኔ ይዛችሁ ኑ” ብሎ ሁለተኛ ደብዳቤ ጻፈላቸው። የንጉሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚያሳድጓቸው በከተማዪቱ ታላላቆች ዘንድ ነበሩ።