የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በአ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ሥር​ዐት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት ባደ​ረ​ጓት ሥር​ዐት ሄደው ነበ​ርና እን​ደ​ዚህ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ከፊታቸው አሳድዶ ያወጣቸውን የአሕዛብንና የእስራኤልም ነገሥታት ወደ ምድሪቱ ያገቡትን አስጸያፊ ልማድ ስለ ተከተሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕዝቡ ወደ ፊት እየገፋ በመጣ ጊዜ ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸውን የአሕዛብን መጥፎ ልማድ ተከተሉ፤ እንዲሁም የእስራኤል ነገሥታት ያሠራጩትን መጥፎ ልማድ ተቀባዮች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕዝቡ ወደ ፊት እየገፋ በመጣ ጊዜ ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸውን የአሕዛብን መጥፎ ልማድ ተከተሉ፤ እንዲሁም የእስራኤል ነገሥታት ያሠራጩትን መጥፎ ልማድ ተቀባዮች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ከእስራኤል ልጆች ፊት ባሳደዳቸው በአሕዛብ ሥርዐት፥ የእስራኤልም ነገሥታት ባደረጓት ሥርዐት ሄደው ነበርና እንደዚህ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 17:8
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም ተማ​ከረ፤ ሁለ​ትም የወ​ርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መው​ጣት ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡ​አ​ችሁ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ እነሆ” አላ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ በዓ​መቱ ወልደ አዴር ሶር​ያ​ው​ያ​ንን ቈጠ​ራ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ይዋጋ ዘንድ ወደ አፌቅ ወጣ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ አካ​ዝም የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን ሊገ​ና​ኘው ወደ ደማ​ስቆ ሄደ፤ በደ​ማ​ስቆ የነ​በ​ረ​ው​ንም መሠ​ዊያ አየ፤ ንጉ​ሡም አካዝ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ምሳ​ሌና የአ​ሠ​ራ​ሩን መልክ ወደ ካህኑ ወደ ኦርያ ላከው።


ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ልጁን በእ​ሳት ሠዋው።


ይሁ​ዳም ደግሞ እስ​ራ​ኤል ባደ​ረ​ጋት ሥር​ዐት ሄደ እንጂ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ አል​ጠ​በ​ቀም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉት።


ነገር ግን እነ​ርሱ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ልማ​ዳ​ቸ​ውን አት​ስሙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ራ​ቃ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።


ምድረ በዳ​ውን ለውኃ መው​ረጃ፥ ደረ​ቁ​ንም ምድር የውኃ ምን​ጮች አደ​ረገ።


ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው አት​ስ​ገድ፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም አት​ሥራ፤ ነገር ግን ፈጽ​መህ አፍ​ር​ሳ​ቸው፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብ​ራ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የአ​ሕ​ዛ​ብን መን​ገድ አት​ማሩ፤ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትም አት​ፍሩ፤ አሕ​ዛብ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ይፈ​ራ​ሉና።


እር​ስ​ዋም ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ ፍር​ዴን በኀ​ጢ​አት ለወ​ጠች፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ከአሉ ሀገ​ሮች ሁሉ ይልቅ ትእ​ዛ​ዜን ተላ​ለ​ፈች፤ ፍር​ዴን ጥለ​ዋ​ልና፥ በት​እ​ዛ​ዜም አል​ሄ​ዱ​ምና።


ኤፍ​ሬም የተ​ገፋ ሆነ፤ በፍ​ር​ድም ተረ​ገጠ፤ ከን​ቱን ይከ​ተል ዘንድ ጀም​ሮ​አ​ልና።


እንደ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባት እንደ ግብፅ ምድር ሥራ አት​ሥሩ፤ እኔም ወደ እር​ስዋ እን​ደ​ማ​ገ​ባ​ችሁ እንደ ከነ​ዓን ምድር ሥራ አት​ሥሩ፤ በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውም አት​ሂዱ።


“ለእ​ና​ንተ በእጅ የተ​ሠራ ጣዖት አታ​ድ​ርጉ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸም ምስል ወይም ሐው​ልት አታ​ቁሙ፤ ትሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም ዘንድ በም​ድ​ራ​ችሁ ላይ የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋይ አታ​ኑሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ እነ​ዚያ አሕ​ዛብ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኵ​ሰት ታደ​ርግ ዘንድ አት​ማር።