የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አካዝ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባ​ቱም እንደ ዳዊት በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በታ​ማ​ኝ​ነት ቅን ነገ​ርን አላ​ደ​ረ​ገም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት ያደረገውን መልካም ነገር በእግዚአብሔር ፊት አላደረገም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ሀያ ዓመት ነበር፤ እርሱም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እርሱም የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት አልተከተለም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ አምላኩን እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ሥራ ሠራ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ኻያ ዓመት ነበር፤ እርሱም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እርሱም የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት አልተከተለም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ አምላኩን እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ሥራ ሠራ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አላደረገም።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 16:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ ባደ​ረ​ገው በአ​ባቱ ኀጢ​አት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም አል​ነ​በ​ረም።


አባ​ት​ህም ዳዊት እንደ ሄደ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ትጠ​ብቅ ዘንድ በመ​ን​ገዴ የሄ​ድህ እንደ ሆነ፥ ዘመ​ን​ህን አበ​ዛ​ል​ሀ​ለሁ።”


ዳዊ​ትም አባ​ትህ በጽ​ድቅ፥ በን​ጹሕ ልብና በቅ​ን​ነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብት​ሄድ፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሕጌ​ንም ብት​ጠ​ብቅ፥


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን አባቱ ኢዮ​አስ እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ እንጂ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አላ​ደ​ረ​ገም።


አባቱ አሜ​ስ​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ አባቱ ዓዛ​ር​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነ​ገሠ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ካዝ ልጅ ሕዝ​ቅ​ያስ ነገሠ።


እር​ሱም አባቱ ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ቀኝም ግራም አላ​ለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ ጋር ነበረ፤ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም በአ​ባቱ በዳ​ዊት መን​ገድ ሄዶ​አ​ልና፥ ጣዖ​ት​ንም አል​ፈ​ለ​ገ​ምና፤


አባ​ቱም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።