Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 14:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን አባቱ ኢዮ​አስ እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ እንጂ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አላ​ደ​ረ​ገም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ፤ ነገር ግን አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ዐይነት አልነበረም፤ በማናቸውም ረገድ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አሜስያስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቶአል፤ ይሁን እንጂ እንደ ቀድሞ አያቱ እንደ ንጉሥ ዳዊት አልነበረም፤ እንደ ዳዊት በመሆን ፈንታ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አሜስያስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቶአል፤ ይሁን እንጂ እንደ ቀድሞ አያቱ እንደ ንጉሥ ዳዊት አልነበረም፤ እንደ ዳዊት በመሆን ፈንታ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን አባቱ ኢዮአስ እንዳደረገ ሁሉ እንጂ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አላደረገም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 14:3
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ ሰሎ​ሞን በሸ​መ​ገለ ጊዜ ልቡ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አል​ነ​በ​ረም። ከባ​ዕድ ያገ​ባ​ቸው ሚስ​ቶ​ቹም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ይከ​ተል ዘንድ ልቡን መለ​ሱት።


አሳም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ ባደ​ረ​ገው በአ​ባቱ ኀጢ​አት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም አል​ነ​በ​ረም።


ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይወ​ድድ ነበር፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ሥር​ዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።


ካህኑ ዮዳሄ ያስ​ተ​ም​ረው በነ​በረ ዘመን ሁሉ ኢዮ​አስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ።


መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ አም​ስት ዓመት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ዮአ​ድም የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች።


ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።


እር​ሱም አባቱ ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ቀኝም ግራም አላ​ለም።


ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም ከሞተ በኋላ የይ​ሁዳ አለ​ቆች ገብ​ተው ለን​ጉሡ ሰገዱ፤ ንጉ​ሡም ሰማ​ቸው።


ኢዮ​አ​ስም በካ​ህኑ በኢ​ዮ​አዳ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


ጌታ ሆይ! አንተ ኀይ​ሌና ረዳቴ፥ በመ​ከ​ራም ቀን መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤ ከም​ድር ዳርቻ አሕ​ዛብ ወደ አንተ መጥ​ተው፥ “በእ​ው​ነት አባ​ቶ​ቻ​ችን ውሸ​ት​ንና ከን​ቱን ነገር ለም​ንም የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን ጣዖ​ትን ሠር​ተ​ዋል” ይላሉ።


ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች