የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ታቦ​ቲ​ቱም በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ከተ​ቀ​መ​ጠ​ች​በት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፤ ሃያ ዓመ​ትም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታቦቱ በቂርያትይዓይሪም ከተቀመጠ ረዥም ጊዜ ሆነው፤ በአጠቃላይ ሃያ ዓመት ቈየ። የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ አዘነ፤ እግዚአብሔርንም ፈለገ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ታቦቱ በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠ ረዥም ጊዜ ሆነው፤ ሃያ ዓመትም ያህል ኖረ። በዚያን ጊዜ የእስራኤል ቤት ሁሉ አዝኖ ጌታን ፈለገ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእግዚአብሔር ታቦት ለረዥም ጊዜ በቂርያትይዓሪም ኖረ፤ ይኸውም ኻያ ዓመት ያኽል ነበር፤ በዚህን ጊዜ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር እጅግ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ታቦቱም በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠበት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፥ ሀያ ዓመትም ሆነ፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግዚአብሔርን ተከተለ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 7:2
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሳ​ኦ​ልም ዘመን ጀምሮ አል​ፈ​ለ​ጓ​ት​ምና የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኛ እን​መ​ል​ሳት” አላ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ያመጡ ዘንድ ዳዊት እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ከግ​ብፅ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ ሰበ​ሰበ።


ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ትን​ቢት የተ​ና​ገረ አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰው የሸ​ማያ ልጅ ኡርያ ይባል ነበር፤ በዚ​ችም ከተማ፥ በዚ​ችም ምድር ላይ እንደ ኤር​ም​ያስ ቃል ሁሉ ትን​ቢት ተና​ገረ።


በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፅሽ፥ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእ​ን​ግ​ዶች እንደ ዘረ​ጋሽ፥ ቃሌ​ንም እን​ዳ​ል​ሰ​ማሽ ኀጢ​አ​ት​ሽን ብቻ ዕወቂ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እያ​ለ​ቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማ​ጽ​ና​ናት አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በወ​ንዝ ዳር በቅን መን​ገድ አስ​ሄ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም አይ​ሰ​ና​ከ​ሉም፤ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አባት ነኝና፥ ኤፍ​ሬ​ምም በኵሬ ነውና።”


የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤መፅናናትን ያገኛሉና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጕ​ዘው በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ደረሱ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ገባ​ዖን፥ ከፊራ፥ ብኤ​ሮ​ትና ኢያ​ሪም ነበሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ይህን ቃል ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ሥ​ተው አለ​ቀሱ።


የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰዎ​ችም መጥ​ተው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ወዳ​ለው ወደ አሚ​ና​ዳብ ቤት አገ​ቡ​አት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት እን​ዲ​ጠ​ብቅ ልጁን አል​ዓ​ዛ​ርን ቀደ​ሱት።


ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​መ​ለ​ሳ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅኑ፤ እር​ሱ​ንም ብቻ አም​ልኩ፤ እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ና​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።