Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 26:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ትን​ቢት የተ​ና​ገረ አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰው የሸ​ማያ ልጅ ኡርያ ይባል ነበር፤ በዚ​ችም ከተማ፥ በዚ​ችም ምድር ላይ እንደ ኤር​ም​ያስ ቃል ሁሉ ትን​ቢት ተና​ገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ደግሞም የቂርያትይዓይሪም ሰው፣ የሸማያ ልጅ ኦርዮ፣ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ ሌላው ሰው ነበር፤ እርሱም እንደ ኤርምያስ በዚህች ከተማና በዚህ ምድር ላይ ትንቢት ተናግሮ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ደግሞም በጌታ ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የቂርያት-ይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፥ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ እንደ ኤርምያስ ቃላት ሁሉ ትንቢት ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በቂርያትይዓሪም የሚኖር የሸማያ ልጅ ኡሪያ የተባለ ሌላም ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ልክ እንደ ኤርምያስ በዚህች ከተማና በዚህች ምድር ላይ ጥፋት እንደሚመጣ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት ተናግሮ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ደግሞም በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የቂርያትይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፥ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ እንደ ኤርምያስ ቃል ሁሉ ትንቢት ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 26:20
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ጌታዬ፥ ይፈ​ል​ግህ ዘንድ ያል​ላ​ከ​በት ሕዝብ ወይም መን​ግ​ሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አን​ተን እን​ዳ​ላ​ገኙ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበር።


አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረጉ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።


ልጆ​ቻ​ች​ሁን በከ​ንቱ ቀሥ​ፌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተግ​ሣ​ጼን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁም፤ ሰይ​ፋ​ችሁ እን​ደ​ሚ​ሰ​ብር አን​በሳ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በል​ቶ​አል፤ በዚ​ህም አል​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝም።


አለ​ቆ​ቹም ባሮ​ክን፥ “አን​ተና ኤር​ም​ያስ ሂዱ፤ ተሸ​ሸጉ፤ ወዴ​ትም እንደ ሆና​ችሁ ማንም አይ​ወቅ” አሉት።


ቴቆ፥ ኤፍ​ራታ፥ ይኽ​ች​ውም ቤተ ልሔም ናት፤ ፋጎ​ርም፥ ኤጣ​ንም፥ ቁሎን፥ ጠጦ​ንም፥ ሶብ​ሄም፥ ቃሬም፥ ጌሌም፥ ኤቴር፥ መነ​ኮም፥ ዐሥራ አንድ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፥ ቅር​ያ​ት​በ​ኣል፥ ይኽ​ች​ውም የኢ​ያ​ርም ከተማ ናት፤ ሶቤታ፥ ሁለቱ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ድን​በ​ሩም ወደ ባሕር ሄደ፤ በቤ​ቶ​ሮ​ንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ አዜብ ዞረ፤ መው​ጫ​ውም ቂር​ያ​ታ​ርም በም​ት​ባል በይ​ሁዳ ልጆች ከተማ በቂ​ር​ያ​ት​በ​ኣል ነበረ፤ ይህ በባ​ሕር በኩል ነበረ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጕ​ዘው በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ደረሱ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ገባ​ዖን፥ ከፊራ፥ ብኤ​ሮ​ትና ኢያ​ሪም ነበሩ።


በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምም ወደ ተቀ​መ​ጡት ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልከው፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት መል​ሰ​ዋል፤ ወር​ዳ​ች​ሁም ወደ እና​ንተ ውሰ​ዱ​አት” አሉ።


ታቦ​ቲ​ቱም በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ከተ​ቀ​መ​ጠ​ች​በት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፤ ሃያ ዓመ​ትም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች