Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰዎ​ችም መጥ​ተው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ወዳ​ለው ወደ አሚ​ና​ዳብ ቤት አገ​ቡ​አት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት እን​ዲ​ጠ​ብቅ ልጁን አል​ዓ​ዛ​ርን ቀደ​ሱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የቂርያትይዓይሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኰረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት። የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የጌታን ታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኮረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት። የጌታን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የቂርያትይዓሪም ሰዎችም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስደው በኮረብታ ላይ ወደሚኖረው አቢናዳብ ተብሎ ወደሚጠራ ሰው ቤት አስገቡት፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን የተለየ እንዲሆን አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት አወጡ፥ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡት፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 7:1
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕቃ የም​ት​ሸ​ከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩ​ስን ነገር አት​ንኩ፤ ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ ራሳ​ች​ሁን ለዩ።


በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምም ወደ ተቀ​መ​ጡት ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልከው፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት መል​ሰ​ዋል፤ ወር​ዳ​ች​ሁም ወደ እና​ንተ ውሰ​ዱ​አት” አሉ።


ድን​በ​ሩም ወደ ባሕር ሄደ፤ በቤ​ቶ​ሮ​ንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ አዜብ ዞረ፤ መው​ጫ​ውም ቂር​ያ​ታ​ርም በም​ት​ባል በይ​ሁዳ ልጆች ከተማ በቂ​ር​ያ​ት​በ​ኣል ነበረ፤ ይህ በባ​ሕር በኩል ነበረ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጕ​ዘው በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ደረሱ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ገባ​ዖን፥ ከፊራ፥ ብኤ​ሮ​ትና ኢያ​ሪም ነበሩ።


ታቦ​ቲ​ቱም በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ከተ​ቀ​መ​ጠ​ች​በት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፤ ሃያ ዓመ​ትም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተለ።


ከሳ​ኦ​ልም ዘመን ጀምሮ አል​ፈ​ለ​ጓ​ት​ምና የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኛ እን​መ​ል​ሳት” አላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች