የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሀ ያደ​ር​ጋል፤ ባለ​ጠ​ጋም ያደ​ር​ጋል፤ ያዋ​ር​ዳል፤ ደግ​ሞም ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ድሀ ያደርጋል፤ ሀብታምም ያደርጋል፤ ያዋርዳል ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ ከፍ፥ ከፍም ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፥ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 2:7
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ገባ፥ ዘይ​ቱ​ንም በራሱ ላይ አፍ​ስሶ እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ።


ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትና ክብር ከአ​ንተ ዘንድ ነው፤ አቤቱ፥ አን​ተም ሁሉን ትገ​ዛ​ለህ፤ የሥ​ል​ጣን ሁሉ ጌታ ነህ፤ ኀይ​ልና ብር​ታት በእ​ጅህ ነው፤ ኀያል ነህ፤ ታላቅ ለማ​ድ​ረግ፥ ለሁ​ሉም ኀይ​ልን ለመ​ስ​ጠት ዓለ​ምን ሁሉ በእ​ጅህ የያ​ዝህ ነህ።


ለሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ ብዙ ሀብ​ትና ክብር ነበ​ረው፤ ለብ​ርና ለወ​ር​ቅም፥ ለከ​በ​ረው ዕን​ቍና ለሽ​ቱው፥ ለጋ​ሻ​ውና ውድ ለሆ​ነው ዕቃ ሁሉ ግምጃ ቤቶ​ችን ሠራ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ብዙ ጥሪት ሰጥ​ቶት ነበ​ርና ከተ​ሞ​ችን ለራሱ ሠራ፤ ብዙም የበ​ግና የላም መንጋ ሰበ​ሰበ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ራቁ​ቴን ወጥ​ቻ​ለሁ፥ ራቁ​ቴ​ንም ወደ ምድር እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጠ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነሣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ብ​ሔር ስም የተ​ባ​ረከ ይሁን።”


ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውን ሰው ዝቅ ዝቅ አድ​ር​ገው፤ ዝን​ጉ​ዎ​ች​ንም በአ​ንድ ጊዜ አጥ​ፋ​ቸው።


የተ​ዋ​ረ​ዱ​ትን ከፍ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፥ የወ​ደ​ቁ​ት​ንም ያነ​ሣ​ቸ​ዋል።


እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችን አላ​ደ​ረ​ገ​ብ​ንም፥ እንደ በደ​ላ​ች​ንም አል​ከ​ፈ​ለ​ንም።


አንተ ግን፥ ግሩም ነህ፤ ቍጣ​ህን ማን ይቃ​ወ​ማል?


ፍር​ድን ከሰ​ማይ ታሰ​ማ​ለህ። ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥


ባለ ጠጋና ድሃ በአንድነት ተገናኙ፤ ሁለቱንም እግዚአብሔር ፈጠራቸው።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በት​ዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውና በኵ​ራ​ተ​ኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለ​ውም ላይ ይሆ​ናል፤ እነ​ር​ሱም ይዋ​ረ​ዳሉ፤


እነሆ በሕ​ዝብ ዘንድ የተ​ጠ​ቃህ፥ በሰ​ዎ​ችም ዘንድ የተ​ና​ቅህ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።


የዱር ዛፎች ሁሉ፥ ረዥ​ሙን ዛፍ ዝቅ ያደ​ረ​ግሁ፥ አጭ​ሩ​ንም ዛፍ ከፍ ያደ​ረ​ግሁ፥ የለ​መ​ለ​መ​ው​ንም ዛፍ ያደ​ረ​ቅሁ፥ የደ​ረ​ቀ​ው​ንም ዛፍ ያለ​መ​ለ​ምሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ርሁ፤ እኔም አደ​ረ​ግሁ።”


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፤ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።