መልአኩም እንዲህ አለው፦ “ከአባትህ ወገን የሆነች ሴት እንድታገባ ብሎ አባትህ የመከረህን ረሳኸው? ስማኝ ወንድሜ! ስለ ጋኔኑ እንደሆነ አትጨነቅ፥ አግባት፤ ዛሬ ማታ ሚስት እንድትሆንህ እንደሚሰጡህ አውቃለሁ።
ወደ ጫጕላ ቤትም በገባህ ጊዜ የዕጣን ዕራሪ ውሰድ፤ ከዚህም ዓሣ ከጉበቱና ከልቡ ጨምረህ አጢስበት።