ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 እኔም ፈርቻለሁ፤ ጋኔኑ ስለሚወዳት እርሷን አይጐዳትም፥ ወደ እርሷ መቅረብ የሚፈልገውን ሰው ግን ወዲያውኑ ይገድለዋል። እኔም ለአባቴ አንድ ልጅ ነኝ መሞትም አልፈልግም፥ አባትና እናቴ በቀሪው ዘመናቸው ሁሉ በእኔ እያዘኑ እንዲኖሩ አልፈልግም። የሚቀብራቸውም ሌላ ልጅ የላቸውም።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ያም መልአክ አለው፥ “ከዘመዶችህ ሚስት ታገባ ዘንድ አባትህ ያዘዘህን ቃል አታስብምን? አሁንም አንተ ወንድሜ ስማኝ፤ የጋኔኑ ነገርስ አያሳዝንህ፤ በዚች ሌሊት ከዘመዶችህ ወገን እርሷ ሚስት ሆና ትሰጥሃለችና፤ ምዕራፉን ተመልከት |