“ከወዴት ነህ ወንድሜ?” አለው። እርሱም “እኔ ከወገኖችህ የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ፤ እዚህ የመጣሁት ለመሥራት ነው” አለው። ጦብያም “ወደ ሜዶን የሚወስደውን መንገድ ታውቀዋለህን?” አለው።
እርሱም አለው፥ “ሀገሩን ታውቅ እንደ ሆነ ወደ ሜዶን ክፍል ወደ ራጊስ ከኔ ጋራ መሄድ ትችላለህን?”