አንተን በድለናል ትእዛዞችህንም አፍርሰናልና፤ ለዝርፊያ፥ ለስደትና ለሞት፥ ተበትነን በምንኖርባቸው አገሮች ሁሉ ተንቀን መተረቻና ማላገጫ እንድንሆን አሳለፈህ ሰጥተኸናል።
ለመበርበርና ለመማረክ፥ ለመገደልም አደረግኸን፤ በዓለሙ ሁሉና በውስጣቸው በተበተንባቸው በአሕዛብም ዘንድ መተረቻና መዘባበቻ ሆንን።