መጽሐፈ ጦቢት 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናትህን እኔ አጠገብ እንደቀበርካት ቀኑ መቼም ይሁን መቼ በዚያኑ ቀን ሂድ፤ ክፋትና፥ ሸፍጥ ያለ ሃፍረት አሸንፎ በማይባት በዚች ከተማ ውስጥ አትቆይ። ልጄ ሆይ በአሳዳጊ አባቱ በአሂካር ላይ ናዳብ ያደረገውን ተመልከት፤ አሂካር በሕይወት እያለ ወደ ጉድጓድ እንዲገባ አልተደረገምን? እግዚአብሔር ግን የጭካኔ ሥራውን በተበዳዩ ዐይን ፊት እንዲከፍል አድርጎታል። ናዳብ አሂካርን ለመግደል ስለፈለገ ተቀጥቶ ወደ ዘለዓለም ጨለማ ወረደ፥ አሂካር ግን ወደ ብርሃን ወጣ፤ በደግ ሥራው ምክንያት አሂካር ናዳብ ካጠመደበት ከሞት ወጥመድ ወጣ፥ ናዳብ ግን ወደ እራሱ ወጥመድ ወደቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አክብረህ ቅበረኝ፤ እናትህንም ከእኔ ጋር ቅበራት። ልጄ፥ በነነዌ አትቈይ። ሐማ በዘመድህ በአኪአክሮስ ያደረገውን፥ ከብርሃን ወደ ጨለማ እንዳገባው፥ ፍዳውንም እንደ ተቀበለ፥ አኪአክሮስም እንደ ዳነ እይ። እርሱ ግን ፍዳውን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ ጨለማ ወረደ። ምናሴ ምጽዋትን አደረገ፤ እውነትንም አደረገ፤ ከመከሩበት ከሞት መቅሠፍትም ዳነ። ሐማ ግን በዚያች ወጥመድ ወደቀና ሞተ። |