መጽሐፈ ጦቢት 13:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊቱ እውነትን የሆነውን ለማድረግ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ንፍሳችሁ ወደ እርሱ ከተመለሳችሁ፥ እርሱም ወደ እናንተ ይመለሳል፥ ፊቱንም ከዚህ በኋላ አይሰውርም። ያደረገላችሁን አስቡ፥ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ ምስጋናን ስጡት፤ የጽድቅ ጌታ ባርኩት፤ የዘመናትንም ንጉሥ አሞግሱት። እኔ ተማርኬ በመጣሁበት አገር ሆኜ፥ ምስጋናውን እዘምራለሁ፤ ኃጢአት በሠራች ከተማ ላይ ኃይሉንና ትልቅነቱን አስታውቃለሁ። ኃጢአተኞች ወደ እርሱ ተመለሱ፥ ስራችሁ በፊቱ ትክክለኛ ይሁን፥ ምናልባት ምሕረት ያደርግላችሁ፥ ይራራላችሁ ይሆናል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በፊቱ እውነትን ትሠሩ ዘንድ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም ወደ እርሱ ከተመለሳችሁ ያን ጊዜ እርሱ ወደ እናንተ ይመለሳል። ፊቱንም ከእናንተ አይሰውርም። ከእናንተ ጋር ያደረገውን ታያላችሁ። በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም እመኑበት፤ ጻድቅ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ የዘለዓለምን ንጉሥ በተማረካችሁበት ሀገር ከፍ ከፍ አድርጉት፤ እኔም በተማረክሁበት ሀገር አምንበታለሁ፤ ኀጢአተኞች ለሆኑ ለአሕዛብም ኀይሉንና ገናናነቱን እናገራለሁ። እናንተ ኀጢአተኞች፥ ተመልሳችሁ በፊቱ እውነትን ሥሯት፤ ወድዶም ቸርነቱን ለእናንተ ያደርግላችሁ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? |