መጽሐፈ ጦቢት 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህን ለካህናቱ ለአሮን ልጆች በመሠዊያው ላይ እሰጥ ነበር። የወይን፥ የእህል፥ የወይራ፥ የሮማንና ሌሎችም ፍሬዎች አስራት በኢየሩሳሌም ለሚያገለግሉ ሌዋውያን እሰጥ ነበር። መሬት በማይታረስበት በሰባተኛው ዓመት ካልሆነ በቀር በየዓመቱ ሁለተኛውን አሥራት በጥሬ ገንዘብ ለውጬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄድና እከፍል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እህሉንና መጀመሪያውን ዐሥራት ሁሉ በኢየሩሳሌም ለሚያገለግሉ ለአሮን ልጆች እሰጣቸው ነበር፤ ሁለተኛውን እጅ ዐሥራት ግን እሸጠው ነበር፤ ምጽዋቱንም አውጣጥቼ በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም እሄድ ነበር። |