ጽዋውን ያነሣል፥ የወይኑንም ጭማቂ በዙሪያው ያፈሳል፥ በመሠዊያው ግርጌ ይረጫል፤ መዓዛውም የዓለምን ንጉሥ ልዑል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል።
የወይኑን ጽዋዕ ይዞ እጁን አነሣ፤ የወይኑን ዘለላ ደምም አፈሰሰ፤ ለንጉሠ ነገሥት ለልዑል በጎ መዓዛ አድርጎ በመሠዊያው እግር ሥር ያፈስሰው ነበር።