እርፍ የሚጨብጥ፥ ፎላጐቱ በዘንጉ መጠቀም የሆነ፥ በሥራ የተጠመዱትን በሬዎች የሚነዳ፥
ዕርፉን የሚያጸና ሰው በምንም አይራቀቅም፥ በእርሻው ይታበያል፥ በሬውንም ይገርፋል፤ በሥራውም ይመላለሳል፤ ነገሩም ሁሉ ስለ በሬና ወይፈን ነው።