ሩት 4:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፥ ሚስትም ሆነችው፥ ወደ እርሷም ገባ፤ እግዚአብሔርም ፅንስ ሰጣት፥ ወንድ ልጅም ወለደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ቦዔዝ ሩትን ወሰዳት፤ ሚስቱም ሆነች። ከዚያም ወደ እርሷ ገባ፤ እግዚአብሔር እንድትፀንስ አደረጋት፤ ወንድ ልጅም ወለደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ሁኔታ ቦዔዝ ሩትን ሚስት አድርጎ ወደ ቤቱ ወሰዳት፤ በተገናኙም ጊዜ እግዚአብሔር ፀንሳ ወንድ ልጅ እንድትወልድ አደረጋት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፥ ሚስትም ሆነችው፣ ደረሰባትም፥ እግዚአብሔርም ፅንስ ለጣት፥ ወንድ ልጅም ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ደረስባትም፤ እግዚአብሔርም ፅንስ ሰጣት፤ ወንድ ልጅም ወለደች። |
ዓይኑን አንስቶም ሴቶችንና ልጆችን ባየ ጊዜ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” አለ። እርሱም፦ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።
አሁንም፥ ልጄ ሆይ! አትፍሪ፤ በከተማው ያሉ ሰዎች ሁሉ አንቺ ምግባረ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ ያውቃሉና ያልሽውን ነገር ሁሉ አደርግልሻለሁ።