Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 30:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፦ በውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ያዕቆብም ራሔልን ተቈጥቶ “እኔ እንዳትወልጂ ያደረገሽን እግዚአብሔርን መሰልኹሽን?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ያዕቆብም ራሔልን ተቈጥቶ “ልጅ ልሰጥሽና ልከለክልሽ የምችል እግዚአብሔር መሰልኩሽን?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ያዕ​ቆ​ብም፥ “የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽን ፍሬ የም​ከ​ለ​ክ​ልሽ እኔ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝን?” ብሎ ራሔ​ልን ተቈ​ጣት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፦ በውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 30:2
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሦራም አብራምን፦ እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ፥ ምናልባት ከእርሷ በልጅ እታነጽ እንደሆነ ወደ እርሷ ግባ አለችው።


እነሆ፥ ልጆች የጌታ ስጦታ ናቸው፥ የማሕጸንም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።


የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቁጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቆዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ።


ሐናንም ይወዳት ስለ ነበር ዕጥፍ ድርሻ ይሰጣት ነበር፤ ይሁን እንጂ ጌታ ማሕፀኗን ዘግቶት ነበር።


ዮሴፍም አላቸው፦ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የምሆን ነኝ?


ተቆጡ፥ ኃጢአትን ግን አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፤


ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ፥ ዙሪያውን በቁጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። እርሱም ዘረጋ፤ እጁም ዳነች።


እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙን ‘የማያስብ’ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ‘ደደብ’ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።


መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት። ሃሌ ሉያ።


እንዲህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃውንና ዘፈኑን አየ፤ የሙሴ ቁጣ ነደደ፥ ጽላቶቹን ከእጁ ወርውሮ ከተራራው በታች ሰበራቸው።


ያዕቆብም ተቆጣ ላባንም ወቀሰው፥ ያዕቆብም ላባንም እንዲህ አለው፥ “ምን በደልሁህ? ይህን ያህል ያሳደድኸኝ፥ ኃጢአቴስ ምንድነው?


እግዚአብሔርም ልያ የተጠላች መሆንዋን ባየ ጊዜ ማኅፀንዋን ከፈተላት፥ ራሔል ግን መካን ነበረች።


ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርሷ ወደ ጌታ ጸለየ፤ ጌታም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤


ጌታ በአብርሃም ሚስት በሣራ ምክንያት በአቢሜሌክ ቤት ማኅፀኖችን ሁሉ በፍጹም ዘግቶ ነበርና።


በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች