Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሩት 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሴቶችም ናዖሚንን፦ “ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ ጌታ ይባረክ፥ ስሙም በእስራኤል ይጠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሴቶቹም ኑኃሚንን እንዲህ አሏት፤ “ዛሬ የሚቤዥ ቅርብ የሥጋ ዘመድ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፤ በመላው እስራኤልም ስሙ ይግነን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሴቶች ናዖሚን እንዲህ አሉአት፦ “ዛሬ ወራሽና ጧሪ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! እግዚአብሔር ይህን ልጅ በእስራኤል ዝነኛ ያድርገው!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሴቶችም ኑኃሚንን፦ ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፣ ስሙም በእስራኤል ይጠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሴቶችም ኑኃሚንን “ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ስሙም በእስራኤል ይጠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሩት 4:14
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ታላቅ ምሕረቱን እንዳደረገላት ሰምተው ከእርሷ ጋር ደስ አላቸው።


አንድም አካል ቢሠቃይ የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሠቃያሉ፤ አንድ አካልም ቢከበር የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።


ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፥ ለበረከትም ትሆናለህ፤


ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ አድጎአልና፥ የእናንተም የእያንዳንዳችሁ ሁሉ ፍቅር ለእርስ በርሳችሁ በዝቶአልና፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግዴታ አለብን፤


በሁሉ ነገር አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።


ደግሞም ፀነስች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፥ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።


እንዲህም አለ፦ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፥ እኔ በመንገድ ሳለሁ እግዚአብሔር ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት መራኝ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች