እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
በእጆቻቸው ያነሡህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል።
እግሮችህ ድንጋይ አደናቅፎአቸው እንዳይጐዱ መላእክቱ በእጆቻቸው ይደግፉሃል።
ጻድቅ ግን እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይበዛል፥
ቃል ኪዳንህ ከምድረበዳ ድንጋይ ጋር ይሆናልና፥ የምድረ በዳም አራዊት ከአንተ ጋር ይስማማሉና።
ቢወድቅም አይጣልም፥ ጌታ እጁን ይዞ ይደግፈዋልና።
የዚያን ጊዜ መንገድህን ተማምነህ ትሄዳለህ፥ እግርህም አይሰነካከልም።
እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁን፥ ስሙኝ።
በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።
“‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ራስህን ወደ ታች ወርውር” አለው።
እግርህም በድንጋይ ከቶ እንዳይሰናከል አንተን በእጃቸው ያነሡሃል፤’ ተብሎ ተጽፎአልና።”