መዝሙር 76:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ፈረሶች አንቀላፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤ በተቈጣህ ጊዜ ማን በፊትህ መቆም ይችላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ አንተ ግን በሁሉ ዘንድ የተፈራህ ነህ፤ አንተ ስትቈጣ በፊትህ የሚቆም አንድ እንኳ አይኖርም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ለዘለዓለም በውኑ ይጥላልን? እንግዲህስ ይቅርታውን አይጨምርምን? |
የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ እንደ ዛሬው እኛ አምልጠን ቀርተናል፥ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፥ በዚህ ምክንያት በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።
በዚያን ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለጌታ ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦ “ለጌታ እዘምራለሁ በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።