መዝሙር 130 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የዕርገት መዝሙር። 1 የዕርገት መዝሙር። አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ። 2 አቤቱ፥ ድምፄን ስማ፥ ጆሮህ የልመናዬን ቃል ያድምጥ። 3 አቤቱ፥ ኃጢአትን ብትይዝ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል? 4 ይቅርታ በአንተ ዘንድ ነውና። 5 አቤቱ ተስፋ አደረግሁ፥ ነፍሴ ጠበቀች፥ በቃሉ ታመንኩ። 6 ማለዳን ከሚጠብቁ የሌሊት ጠባቂዎች ይልቅ፥ ነፍሴ ጌታን ትጠብቃለች፥ ማለዳን ከሚጠብቁ ጠባቂዎች ይልቅ። 7 ከጌታ ጋር ጽኑ ፍቅር፥ በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን አለና እስራኤል በጌታ ይታመን። 8 እርሱም እስራኤልን ከበደሉ ሁሉ ያድነዋል። |