መዝሙር 57:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማረኝ፥ አቤቱ፥ ማረኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፥ ጉዳት እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእኔ ያሰበውን ወደሚፈጽምልኝ አምላክ፣ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያስፈልገኝን ሁሉ ወደሚሰጠኝ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጣራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልባችሁ በምድር ላይ ኀጢአትን ትሠራላችሁና፥ እጆቻችሁም ሽንገላን ይታታሉና። |
ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።
ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ ይበልጥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።