Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 13:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሠኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን። አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ፈቃዱን ለመፈጸም እንድትበቁ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሰኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለኢየሱስ ክርስቶስም ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የሰ​ላም አም​ላክ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን በእ​ና​ንተ እያ​ደ​ረገ ፈቃ​ዱን ታደ​ርጉ ዘንድ በመ​ል​ካም ሥራ ሁሉ ፍጹ​ማን ያድ​ር​ጋ​ችሁ፤ ለእ​ርሱ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 13:21
53 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጎ ፈቃዱን እንድትፈልጉና እንድታደርጉ ሁለቱንም በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።


ልባችሁን ያጽናናው፥ በቃልና በመልካም ሥራ ሁሉ ያጽናላችሁም።


ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለማቅረብ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ እርሱም ለሰማያዊው መንግሥቱ እንድሆን ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኝ የጽድቅ ፍሬ የተሞላችሁ እንድትሆኑ ነው።


ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን አግኝታችሁ በበጎ ሥራ በቸርነት እንድትለግሱ፥ እግዚአብሔር ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።


ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት አትኑሩ።


የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ ጽናት ያስፈልጋችኋል።


የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።


እርሱ ብቻ አዳኛችን ለሆነው አምላክ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ክብር፥ ግርማ፥ ኃይልና ሥልጣን ከዘመናት ሁሉ በፊት፥ አሁንም እስከ ዘለዓለምም ድረስ ይሁን፤ አሜን።


ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዓለም ይኖራል።


ለዘመናትም ንጉሥ፥ ለማይሞተው፥ ለማይታየው፥ ብቻውን አምላክ ለሆነው መፈራትና ክብር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።


እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ በሕይወት እንድንመላለስ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።


“እርሱ ዐለት፥ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፥ የታመነ አምላክ፥ ተንኮል የሌለበት፥ እርሱ ቀጥተኛና ጻድቅ ነው።


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


ትእዛዛቱን ስለምንጠብቅ፥ በፊቱም ደስ የሚያሰኘውን ስለምናደርግ፥ የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።


እንዲሁም መልካም ማድረግንና ያላችሁን ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ። እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ለእርሱ ክብርና የዘለዓለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።


እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በበጎም ሥራ ሁሉ በመትጋት፥ በመልካም ሥራዎችዋ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ጌታችን ኢየሱስ በሚመጣበት ጊዜ በአባታችንና በአምላካችን ፊት ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ በቅድስና ልባችሁን ያጽና።


ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል።


በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።


ነገር ግን የሚያስፈልገኝን ሁሉ ተቀብያለሁ፤ ተትረፍርፎልኛልም፤ መዓዛው ያማረ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከኤጳፍሮዲጡስ ተቀብዬ በሁሉ ተሟልቶልኛል።


በእርሱም አማካኝነት ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት እንችላለን።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’


ጌታ ብድራትን ይመልስልኛል፥ አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ ለዘለዓለም ነው፥ አቤቱ፥ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።


በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ “ውዳሴ ገናናነት ክብርም ኃይልም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፤” ሲሉ ሰማሁ።


በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።


በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥


ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፥ እርሱም መቀደሳችሁ፥ ከዝሙትም መራቃችሁ ነው፤


ልጆች ሆይ! ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።


መላስ ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ እንዲመሰክሩ ነው።


ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


ሁሉም ከእርሱ፥ በእርሱና ለእርሱም ነውና፤ ክብር ለዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።


እርሱ ብቻ ጥበበኛ ለሆነው አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ ለዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


ይህም እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በፍጹም አንድ እንዲሆኑ፥ እንዲሁም አንተ እንደ ላክኸኝና በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ዓለም እንዲያውቅ ነው።


ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር እንደሆነ ወይንም እኔ ከራሴ የምናገር እንደሆነ ያውቃል።


ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው የትኛው ነው?” እነርሱም “የመጀመሪያው” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ዘማውያን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል።


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም እንጂ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት አይገባም።


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ፥ እኅቴም እናቴም ነውና።”


ደግሞም አንድ ልብ እንዲሰጣቸው፥ በጌታም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የሹማምንቱን ትእዛዝ እንዲያደርጉ የጌታ እጅ በይሁዳ ላይ ነበረ።


በዚህም የእግዚአብሔር ሰው በችሎታው ፍጹም እንዲሆንና ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ይጠቅማል።


ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች