Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 17:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፥ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የዐይን ብሌን በጥንቃቄ የሚጠበቀውን ያኽል ጠብቀኝ፤ በጥበቃህ ውስጥ ሰውረኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከቍ​ጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊ​ቱም እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእ​ርሱ በራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 17:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዳዊት ቅኔ። አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።


ጽድቅህም እንደ እግዚአብሔር ተራሮች፥ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ናት፥ አቤቱ፥ ሰውንና እንስሳን ታድናለህ።


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን እንዴት አበዛህ! የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።


ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።


ማረኝ፥ አቤቱ፥ ማረኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፥ ጉዳት እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።


በጠላት ፊት ጽኑ ግንብ፥ መጠጊያዬም ሆነኸኛልና።


በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፥ በክንፎችህም ጥላ እጋረዳለሁ፥


በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም ስለ አንተ አሰላስላለሁ፥


በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።


በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ ከክንፎቹም በታች ትጠለላለህ፥ ታማኝነቱ እንደ ጋሻና እንደ ቅጥር ይከብብሃል።


ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፥ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፥


“ሩጥ፥ ይህንም ጎልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ትሆናለች።


“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድዪ ወደ አንቺ የተላኩትንም የምትወግሪ፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ልሰበስብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።


ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም! ነቢያትን የምትገድል፥ ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።


“በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት በምድረ በዳ አገኘው፥ መከታ ሆነለት፥ ተጠነቀቀለትም፥ እንደ ዐይን ብሌኑም ጠበቀው።


ለሠራሽው ሥራ ጌታ ይክፈልሽ፥ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በጌታ ዘንድ ዋጋሽ ፍጹም ይሁን” አላት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች