ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ለመብላት በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።
ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣ እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ።
ክፉ ሰዎች ሲያጠቁኝና ሊገድሉኝ ሲቃጡ እነርሱ ራሳቸው ተሰናክለው ይወድቃሉ።
በቤተ መቅደስህ እጆችን ባነሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።
ስለምን እናንተ እንደ እግዚአብሔር ታሳድዱኛላችሁ? ከሥጋዬስ ስለምን አትጠግቡም?”
በድንኳኔ ሥር የሚኖሩ ሰዎች፦ ‘በሥጋ ያልጠገበ ማን ይገኛል?’ ይሉ የለምን?
ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንደሚነድድ ነደዱ፥ በጌታ ስም አጠፋኋቸው።
ክፉ አድራጊዎች አያስተውሉምን? እንጀራን እንደሚበሉ ሕዝቤን የሚያኝኩ፥ ጌታን አይጠሩምን፥
ምስጋና የሚገባውን ጌታን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጉሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አፈር አወረድኸኝ።
የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
ሁሉም በደሉ፥ አብረውም ረከሱ፥ አንድ እንኳ በጎን ነገር የሚያደርጋት የለም።
እደሰታለሁ፥ በአንተም ሐሤትን አደርጋለሁ፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።
ከእነርሱ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ ይወድቃሉ፤ ይሰበራሉ፤ ወጥመድ ይገባሉ፤ ይያዛሉም።”