Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 22:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጉሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አፈር አወረድኸኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ውሾች ከበቡኝ፤ የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፏል፤ እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ክፉ ሰዎች እንደ ውሻ ስብስብ ከበቡኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 22:16
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግሞም ሌላው የመጽሐፍ ክፍል “ያንን የወጉትን ያዩታል” ይላል።


ከሰቀሉትም በኋላ ልብሶቹን ዕጣ ጥለው ተካፈሉት፤


በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ሌሎቹም ደቀመዛሙርቱ “ጌታን አይተነዋል፤” አሉት። እርሱ ግን “የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ላይ ካላየሁ፥ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ውስጥ ካላስገባሁ፥ እጄንም በጎኑ ቊስል ውስጥ ካላስገባሁ አላምንም፤” አላቸው።


ወታደሮቹም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ወታደር አንድ ክፍል እንዲደርስ በአራት ከፋፈሉአቸው፤ እጀ ጠባቡንም እንዲሁ ወሰዱ። እጀ ጠባቡ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም።


ከዚያም ሰቀሉት፤ እያንዳንዱም ምን እንደሚደርሰው ለማወቅ ዕጣ ተጣጥለው ልብሱን ተከፋፈሉ።


ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ።


ቀራንዮ ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ እርሱን፥ ክፉ አድራጊዎቹንም አንዱን በቀኙ አንዱን በግራው በኩል ሰቀሉ።


ከውሾች ተጠበቁ፤ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፤ ከሐሰተኛም መገረዝ ተጠበቁ።


እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጥብቀው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ድምፅ በረታ።


እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።


አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ፥ አንተ ጉልበቴ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።


ለመዘምራን አለቃ ስለ ንጋት ኃይል፥ የዳዊት መዝሙር።


ከዚያም በኋላ ቶማስን “ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ ውስጥ አስገባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን፤” አለው።


አንተም አቤቱ፥ የኃያላን አምላክ፥ የእስራኤል አምላክ፥ አሕዛብን ሁሉ ትጐበኛቸው ዘንድ ተነሥ፥ ክፉ ከዳተኞችን ሁሉ አትማራቸው።


ውሻዎችና አስማተኞች፥ ሴሰኛዎችም፥ ነፍሰ ገዳዮችም፥ ጣዖት አምላኪዎችም፥ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ ይቀራሉ።


አቤቱ፥ ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፥ የክፉዎችም ማኅበር ነፍሴን ፈለጉአት፥ ላንተም ምንም ቦታ የላቸውም።


ኢየሱስን የያዙት ሰዎች፥ ጻፎችና ሽማግሌዎች ወደ ተሰበሰቡበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወሰዱት።


በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።


ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፤ በመልካምም ቢናገሩህም አትመናቸው።”


በቁጣ አጥፋቸው፥ እንዳይኖሩም አጥፋቸው፥ የያዕቆብም አምላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንደሚገዛ ይወቁ።


ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኃይሌም ተወችኝ፥ የዐይኖቼም ብርሃን ፈዘዘ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች