መዝሙር 127:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ማለዳ መነሣታችሁ፥ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው። እርሱ ለሚወዱት እንቅልፍን ይሰጣልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዕለት ጕርስ ለማግኘት በመጣር፣ ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤ እርሱ ለሚወድዳቸው እንቅልፍን ያድላልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የድካምህን ፍሬ ትመገባለህ፤ ብፁዕ ነህ፥ መልካምም ይሆንልሃል። |
አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።