Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 60:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው፥ አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣ በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስልንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የምትወደው ሕዝብህ ከጒዳት እንዲድን በኀይልህ ታደገን፤ ጸሎታችንን ስማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አም​ላኬ፥ አንተ ጸሎ​ቴን ሰም​ተ​ሃ​ልና፤ ለሚ​ፈ​ሩ​ህም ርስ​ትን ሰጠ​ሃ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 60:5
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚያምኑህን ከሚቃወሙ በቀኝህ የምታድናቸው፥ ቸርነትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሀለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፥ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።


ቀኝህ ጌታ ሆይ፥ በኃይል ታላቅ ነው፤ አቤቱ፥ ቀኝህ ጌታ ሆይ፥ ጠላትን አደቀቀ።


እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆ ከደመናው ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የተወደደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።


እጅህንም ለምን ትመልሳለህ? ቀኝ እጅህንም ለምን በብብትህ መካከል ታቆያለህ?


አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።


እነሆ፥ ከሰማያት ድምፅ ወጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


“ክፋትን አብዝታ በመሥራትዋ ወዳጄ በቤቴ ውስጥ ምን አላት? የተቀደሰ ሥጋ ክፋትሽን ከአንቺ ያስወግዳልን? ከዚያም ደስተኛ ትሆኛለሽን?”


እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ማለዳ መነሣታችሁ፥ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው። እርሱ ለሚወዱት እንቅልፍን ይሰጣልና።


የሚያዩኝ ሁሉ ያፌዙበኛል፥ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይሳለቃሉ፦


በማዳንህ ደስ ይለናል፥ በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፥ ልመናህን ሁሉ ጌታ ይፈጽምልህ።


ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ “በጌታ የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ ቀኑን ሁሉ ይጠብቀዋል፤ በትከሻዎቹም መካከል ያርፋል።”


በእርግጥ ሕዝቡን ይወዳል፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጁ ናቸው፤ እነርሱም በእግሮችህ ሥር ይሰግዳሉ፤ መመሪያህንም ከአንተ ይቀበላሉ።


ብዙ ጭንቀትንና መከራን አሳይተኸኛልና፥ ተመለስህ ሕያውም አደረግኸኝ፥ ከምድር ጥልቅም እንደገና አወጣኸኝ።


ጽዋ በጌታ እጅ ነውና፥ ኃይለኛ የወይን ጠጅ ሞላበት፥ ከዚህ ወደዚያ አገላበጠው፥ ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፥ የምድር ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል።


ከጌታ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ! ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች